Logo
News Photo

ለድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች የህይወት ክህሎት ስልጠና ተሰጠ

በስልጠናው መክፍቻ ላይ ተገኝተው ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች መልዕክታቸውን ያስተላለፉት በዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶ/ር መገርሳ ቃሲም ናቸው፡፡

ዶ/ር መገርሳ በመልዕክታቸው ተማሪዎች በቀዳሚነት ለትምህርታቸው ትኩረት በመስጠት ውጤታማ መሆን ይጠበቅባቸዋል ብለዋለወ፡፡

በተለይም ከመጡበት ዓላማ ከሚያስቷቸው ጎጂ ተግባራት ራሳቸውን ጠብቀው ከራሳቸው አልፈው ለአገራቸው ጠቃሚ ዜጋ መሆን ይገባቸዋል ሲሉ መልእክታቸውን በማስተላለፍ የረጅም ግዜ ህልማቸውን ለማሳከት ዩኒቨርሲቲውን በመምረጣቸው ለተማሪዎች ምስጋና አቅርቧል።


በዩኒቨርሲቲው የሴቶች እና ወጣቶች ኤች አይ ቪ ኤድስ እና ልዪ ፍላጎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ተወካይ ወ/ሪት አዜብ ጌቱ በበኩላቸው አዲስ ገቢ ተማሪዎች ለቅጥር ግቢው አዲስ እንደመሆናቸው ችግር እንዳገጥማቸው ዩኒቨርሲቲው አስፈላጊውን ሁሉ ዝግጅት አድረጓል ብለዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ተማሪዎች በትምህርታቸው ውጤታማ መሆን እንዲችሉ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው የተለያዩ እገዛዎችን ያደርጋል ብለዋል፡፡

ሶስት ቀናት በቆየው ስልጠና ለተማሪዎች ስለ መወጫ ፈተና፣ ስነተዋልዶ፣ አጠቀላይ መማር ማስተማር ላይ፣ የተማሪዎች መብት፤ ግዴታ እና በመሳሰሉት ርዕሶች ዙሪያ በመምህራን የግንዛቤ ስልጠና ተሰቷቸዋል።

Share This News

Comment