Logo
News Photo

በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የማኀበረሰብ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ ለመምህራንና ለተማሪዎች እውቅና ሰጠ፡፡

ማኀበረሰብ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ ለመምህራንና ለተማሪዎች ባዘጋጀው ዕውቅና በመርሐ ግበር ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር መገርሳ ቃሲም እንደገለፁት የ2015 ዓ/ም ተሞክሮ በመቀመር በዘንድሮ ዓመት የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ኮሌጁ እና ትምህርት ክፍሎች ስራቸውን በዕቅድ እንዲመሩ አሳስበው፣ ተማሪዎችም የሚሰጣቸውን ድጋፍ በአግባቡ መጠቀም እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል፡፡


የኮሌጁ ዲን ዶ/ር መዓዛሽወርቅ በበኩላቸው እንደገለጹት የ2015 ዓ.ም የመውጫ ፈተና አጠቃላይ ሂደት ላይ ባቀረቡት አጭር ጽሑፍ  የተገኘው ውጤት እንደ ኮሌጅ ጥሩ የሚባል ነው፡፡ ይኹን እንጅ የበለጠ መሥራት እንደሚገባ አመላካች መሆኑን ጠቁመዋል፡፡  

ተማሪዎችም የራሳቸውን ድርሻ እንዲወጡ ግንዛቤ መፍጠር ስለሚገባ መድረኩ እንደተዘጋጀም ገልጸዋል፡፡ 

በተያዘው ዓመትም የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ በዕቅድ ላይ የተመሠረተ ሥራ መጀመሩን የገለፁት ዶ/ር መዓዛሽወርቅ እነዚሁ ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ሲሉ አረጋግጠዋል፡፡


በመጨረሻም ለሥራው የላቀ አስተዋፅኦ ለነበራቸው መምህራን፣ በትምህርታቸው ጥሩ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የእውቅና ምስክር ወረቀት እና የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

Share This News

Comment