Logo
News Photo

የኤች .አይ. ኤድስና የነጭ ሪቫን ቀን በድሬደዋ ዩኒቨርሲተ ተከበረ፡፡

ከህዳር 15 እስከ ህዳር 30 ቀን በአለም አቀፋ ደረጃና በሃገራችን "የእኛ ሰላም ይስፈን በሴቶችና በህፃናት ላይ የሚፈፀም ጥቃት ይቁም" በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል፡፡


የአለም አቀፉን የኤች.አይ.ቪ ኤድስና የነጭ ሪቫን ቀን  በማስመልከትም በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ የሴቶችና ወጣቶችና ኤች .አይ.ቪ. ኤድስ እና ልዩ ፍላጎት ዳይሬክቶሬት የዩኒቨርሲቲው መምህራንና የአስተዳደር ሠራኞች የተሳተፉበት የውይፍት መድረክ አካሂዷል፡፡


በዚሁ መድረክ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም እንደገለጹት በቅርብ የተደረጉ ጥናቶችና መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በሴቶች ላይ የሚፈፀም ጥቃት ሴቶችን ለተለያዩ ውስብስብ ችግሮች ከማጋላጡም ባለፈ  በሃገራችን የኤች. ኤይ.ቪ ኤድስ በደማቸው ከሚገኝባቸው ሰዎች መካካል አብዛኛውን ቁጥር ሴቶች እንዲይዙ ማድረጉን ገልፀዋል፡፡

ይህን በሁለንተናዊ መልኩ የሚደርሰውን ጫና በመቀነስ ሴቶች በማህበራዊ ፣ በምጣኔ ሃብታዊው ዘርፍ ተጠቃሚ ለማድረግ እና በፖለቲካው መስክ ተሳታፊ እንዲሆኑ ለማስቻል የወንዶች ሚና ትልቅ ድርሻ ነው የሚኖረው ያሉት ዶ/ር ኡባህ ወንዶች በሴቶች ላይ ጥቃትን ባለመፈፀምና እንዳይፈፀም በመከላከል እና ተፈፅሞ ሲገኝም ፈፃሚዎችን በማጋለጥ በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ስኬታማ እንዲሆን የአንበሳውን ድርሻ ወስደው መንቀሳቀስ ይጠበቅባቸዋል ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡


በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ የሴቶች ወጣቶችና ኤች .አይ.ቪ. ኤድስ እና ልዩ ፍላጎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ይታገሱ ፍቃዱ በበኩላቸው እንደገለጹት የሴቶችን ጥቃት በሚቀንስ መልኩ አጠቃላይ የዩኒቨርሲቲውን ማህበረሰቡ ግንዛቤ እንዲያገኝ የተለያዩ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ጠቁመው በዚህ መድረክ ላይ በሚቀርቡት ጥናታዊ ጽሁፎች ተሳታፊዎችን ግንዛቤ ለማሳደግ ጥረት ይደረጋል ብለዋል፡፡

ለአንድ ቀን በቆየው የውይይት መድረክ ላይ የሴቶች ጥቃት አሁን ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ እና የኤች .አይ.ቪ ኤድስ ስርጭትን የተመለከቱ ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው በመድረኩ ተሳታፊዎች ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን የዩኒቨርሲቲው ሠራተኞችና መምህራንም የኤች. አይ.ቪ የደም ምርምራ አድርገዋል፡፡  

  

ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የዩኒቨርሲቲያችን ትክክለኛ የማህበራዊ ትስስር ገፆች Like እና Subscribe በማድረግ ይከታተላሉ፡-

Share This News

Comment