Logo
News Photo

ሙስናን መከላከል ላይ ትኩረት አድርጎ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡

በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በምስራቁ የአገራችን ክፍል ከሚገኙ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ለተውጣጡ የትምህርት አመራሮች እና በየደረጃው ለሚገኙ የአስተዳደር ሠራተኞ ሙስናንና ብልሹ አሰራርን መከላከል ላይ ትኩረት አድርጎ ለሁለት ቀን የቆየ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡


የፌደራል ስነ-ምግባርንና ፀረሙስና  ኮሚሽን ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በትብብር ያዘጋጁትን የስልጠና መድረክ በንግግር የከፈቱት የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በከፍተኛ በጀት ግዢ የሚፈፅሙ እንደመሆናቸው በዚሁ ወቅት በሙስና ሳቢያ የአገር ሃብት እንዳይመዘበር ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባቸዋል፡፡


በተለይም ግዢ በሚፈፅም ጊዜ የመንግስት ደንብና መመሪያ በሚያዘው መሠረት ብቻ ግዢ እንዲፈፀም  ሙስናንና ብልሹ አሰራርን ከመከሰቱ አሰቀድሞ መከላከል እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

ለዚህ ደግሞ በየደረጃው የሚገኘው የትምህርት አመራር የአስተዳደር ሠራተኛ ሙስናን በመከላከል ረገድ በቂ ግንዛቤ ሊኖረው ይገባል ብልዋል፡፡


ለሁለት ቀን በቆየው ስልጠና ላይ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ ከቀብሪዳህር ፣ ከጅግጅጋ ከሀረማያ እና ከኦዳቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ለተውጣጡ ተሳታፊዎች  የግዢ ስርዕትና የስነ-ምግባር አመራርን አስመልክቶ ከፌደራል ፀረ-ሚስና ኮምሽን በመጡ አሰልጣኞች ስልጠና ተሰጥቷቸዋል፡፡

Share This News

Comment