Logo
News Photo

በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የተንቀሳቃሽ ኢግዚቢሽንና ሲንፖዚየም ተከፈተ

የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር " ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛ " በሚል የተዘጋጀው ተንቀሳቃሽ ኢግዚቢሽንና ሲንፖዚየም ዛሬ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተከፍቷል፡፡


ይህንኑ አስመልክቶ የተዘጋጀውን ሲንፖዚየም የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ተወካይ ዶ/ር መገርሳ ቃሲም ሲከፍቱ እንዳሉት የዚህ አይነቱ ፕሮግራም በዩኒቨርሲቲው መዘጋጀቱ ተማሪዎች በአገራቸው ስለሚገኙ ቅርሶች እንዲያውቁም ብሎም በማስተዋወቁ እና በመንከባከቡ ረገድም የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ የሚያደርግ ነው ብለዋል፡፡


በኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን የሚዚየም ዘርፍ ም/ዳይሬክተር አቶ ኤልያስ ሽኩር በበኩላቸው በድሬዳዋና በአካባቢዋ ያሉትን ቅርሶች በማስተዋወቅና ለቅርሶቹ የሚሰጠው ትኩረት ከመጨመር አኳያ ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ እያደረገያለው አስተዋፆኦ የሚበረታታና ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል፡፡


ከታህሳስ 12 እስከ ታህሳስ 16/2016 ዓ.ም ለተከታታይ 5 ቀን በሚቆየው የተንቀሳቃሽ ኢግዚቢሽን ላይ የሉሲ (ድንቅነሽ) ጨምሮ በተለያዩ ጊዜ በቁፋሮ የተገኙ ጥንታዊ ቅሪተ አካላት እንዲሁም ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ ቅርስንት ያስመዘገበቻቸው የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ጥንታዊ ቅርሶች በፎቶ ተደግፈው  ለእይታ በመቅረብ እየተጎበኙ ይገኛሉ፡፡


Share This News

Comment