Logo
News Photo

የዲጂታል የትምህርት አሰጣጥን አስመልክቶ  ለመምህራን ስልጠና ተሰጠ ፡፡

በድሬዳዋ ዩንቨርስቲ የዲጂታል የትምህርት ስርዓትን ለመዘርጋት የተለያዩ እንቅስቃሴዎች ተጀምረዋል፡፡

በዚህ ረገድ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር ከማስተርካርድ ፋውንዴሽን /Mastercard Foundation፣ ከአሪዞና ስቴት ዩኒቨርሲቲ /Arizona State University ከ50ዎቹ የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት) ጋር በመሆን እየተገበረ ያለው ኢ-ለርኒንግ ( e-SHE) /e-Learning for Strengthening Higher Education/ የተሰኘው የአምስት ዓመት ፕሮጀክት ተጠቃሽ ነው፡፡

የዚሁ ፕሮጀክት አንድ አካል የሆነው ስልጠና  ለድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የMathematics, Computer Science, Information Technology, Software Engineering እና Electrical and Computer Engineering (Computer Stream) ትምህርት ክፍል መምህራን ተሰጥቷል፡፡

ስልጠናውን የሰጡት በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ኢለርናንግ ዳይሬክተር ዶ/ር ተስፉ ጌትዬ እንዳሉት በዩኒቨርስቲው የመማር ማስተማሩን ሂደቱን በዲጀታል ስርዕት ለማዘመን /e-SHE/ ፕሮጀክት ለማዘመን እየተሰሩ የሚገኙ ስራዎች በተሳካ ሁኔታ እየተከናዎኑ ይገኛሉ፡፡

ከእነዚህ ተግባራት መካከል የdigital content የተዘጋጀላቸውን የ Mathematics for Natural Science እና Emerging Technology ኮርሶችን በያዝነው የትምህርት ዓመት ለ1ኛ ዓመት የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ወሰነ ትምህርት ተማሪዎች በblended (face-to-face እና online) የመማር ዘዴ መስጠት አንዱ ነው፡፡

ይህንን የተያዘውን እቅድ ለማሳካት እነዚህን ኮርሶች ለሚያስተምሩ የMathematics, Computer Science, Information Technology, Software Engineering እና Electrical and Computer Engineering (Computer Stream) ትምህርት ክፍል መምህራን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በe-learning director እና AVP ትብብር መሰጠቱን አብራርተዋል፡፡  

በቀጣይም መሰል ስልጠናዎች ለተለያዩ የትምህርት ክፍል መምህራን የሚሰጥ መሆኑን አስተባባሪው ዶ/ር ተስፉ ጌትዬ ጨምረው ገልፀዋል፡፡


Share This News

Comment