Logo
News Photo

ለጆርናሊዝምና ኮሚኒኬሽን ተመራቂ ተማሪዎች መሠረታዊ የፎቶ ፣ የቪዲዮ ግራፊ ፣ የምስልና የድምጽ ቅንብር ስልጠና ተሰጠ፡፡

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ  አፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ከመሆኑ አንፃር በድሬደዋ አስተዳደር ከሚገኙ የተለያዩ ኢንዱስትሪዎች ጋር ትስስር በመፍጠር ተግባር ተኮር ስልጠና በጋራ የመስጠት እንቅስቃሴ መጀመሩ ይታወሳል፡፡ የኢንዱስትሪ ትስስር ማዕቀፍ አንድ አካል የሆነው ባለሙያዎችን ከኢንዱስትሪው በመጋበዝ የተግባር ስልጠና ለተማሪዎቻችን መስጠት አንዱ ተልዕኮ በመሆኑ የዩኒቨርሲቲው የጆርናሊዝምና ኮሚኒኬሽን ትምህርት ክፍል የመጨረሻ ዓመት ተመራቂ ተማሪዎች የፎቶ ፣ የቪዲዮ ግራፊ እና የምስልና የድምፅ ቅንብር  ከኢንዱስትሪው በተጋበዙ ባለሞያዎች ስልጠና እንዲወስዱ ተደርጓል፡፡ 

ለአምስት ቀናት በቆየው ስልጠና በሞያው የረጅም ጊዜ ልምድ ባላቸው የድሬዳዋ አስተዳደር መንግስት ኮሚኒኬሽን ባለሞያዎች ተግባር ተኮር ስልጠና የተሰጠ ሲሆን ስልጣኝ ተማሪዎች የፎቶ ፣ የቪዲዮ ግራፊ ፣ የምስልና የድምጽ ቅንብር አስመልክቶ መሠረታዊ የሆነ ክህሎቶች እንዲጨብጡ ተደርጓል፡፡

በስልጠናውም ማጠቃለያ እንደተገለፀው በተለይ እንዲህ አይነት ስልጠናዎች ለተመራቂ ተማሪዎች በተግባር እውቀትን እንዲቀስሙ እና በሚሰማሩበት የስራ መስክ ብቁና ተወዳደሪ እንደሚያደርጋቸው እሙን በመሆኑ በቀጣይም ተመሳሳይ የትስስር ስልጠናዎች  በተቻለ አቅም ሁሉ እንዲቀጥሉ እንደሚደረግ የስልጠናው አስተባባሪዎች ገልጸዋል፡፡

Share This News

Comment