Logo
News Photo

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎችን መቀበል ጀመረ፡፡

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በዛሬው ዕለት መቀበል የጀመራቸው ተማሪዎች በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው የ remedial ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ እና በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ እና ትምህርታቸውን የሚከታተሉ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ቅበላ፣ የአካዳሚክ ሪከርድ እና አልሙኒ ዳይሬክቶሬት አስታውቋል፡፡

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ቅበላ፣ የአካዳሚክ ሪከርድ እና አልሙኒ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ጂብሪል አብዱልቃድር በዘንድሮ ዓመት በዩኒቨርሲቲው በሪሚዲያል ፕሮግራም 2 ሺህ 9 መቶ 66 ተማሪዎችን ለመቀበል የታቀደ መሆኑን ገልፀው ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ ሥስት ቀናት ምዝገባ የሚካሄድ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

Share This News

Comment