Logo
News Photo

በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት የተመራ የልዑካን ቡድን ቀልዕድ ጥብቅ የዱር እንስሳት መኖርያ ስፍራ ጎበኘ፡፡

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም ፣ የዩኒቨርሲቲው ም/ፕሬዝዳንቶች ፣ የኮሌጅ ዲኖች ፣በተለያዩ የኃላፊነት ቦታ ላይ የሚሠሩ ዳይሬክተሮች  እና የድሬዳዋ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ተወካዮች የቀልዕድ ጥብቅ የዱር እንስሳት መኖሪያን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡


በጉብኝቱ ማብቂያ ላይ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም እንደተናገሩት በድሬዳዋና በዙሪያዋ የሚገኙ እምቅ የቱሪዝም ሃብቶች በአግባቡ ተገንዝቦና ትኩረት ሰጥቶ ጥቅም ላይ እንዲውሉ የሁሉም ማህበረሰብ ያልተቋረጠ አስተዋፅኦ ይፈልጋል፡፡

ከዚህ አንፃርም የቀልዕድ ጥብቅ የዱር እንስሳት መኖሪያ ስፍራ እውቅና አግኝቶ የቱሪስት ምስህብ እንዲሆን ለማስቻል የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በራሱ ተነሳሽነት የአስተዳደሩን ባህልና ቱሪዝም ፅ/ቤትን በማስተባበር ብዙ ርቀት መጓዙን ተናግረዋል፡፡


እነዚህ እንቅስቃሴዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ያሉት ዶ/ር ኡባህ በተለይም የዩኒቨርሲቲው መምህራንና ተመራማሪዎች በአካባቢያችን ያሉ ሃብቶች ላይ ፕሮጀክቶችን ቀርፀው ጥናትና ምርምሮችን በማድረግ ጥቅም ላይ በማዋል የቱሪዝሙን ዘርፍ በማሳደግ ረገድ የበኩላቸውን እንዲወጡ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡


የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ የኮሌጅ ዲኖች፣ በተለያዩ የኃላፊነት ቦታ ላይ የሚሠሩ ዳይሬክተሮች የቀልዕድ ጥብቅ የዱር እንስሳት መኖሪያ፣ የአርሙካሌ የተፈጥሮ ፍል ውኃ እና የታሪካዊቷ የቀልዕድ አነስተኛ ከተማን ተዘዋውረው ጐብኝተዋል።


Share This News

Comment