Logo
News Photo

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ለድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሲስተም ሶፍትዌር ለማበልፀግ የስራ ውል ስምምነት ፈፀመ፡፡

ዩኒቨርሲቲያችን በድሬዳዋ አስተዳደር ስር ባሉ ቢሮዎች እና ተቋማት ጋር በዘረፈ ብዙ ጉዳዮች ላይ በትብብር እየሰራ ይገኛል፡፡ ከእነዚህ ቢሮዎች አንዱ የትምሀርት ቢሮ ሲሆን በ2015 ዓ.ም የበጀት ዓመት ከ1972 ዓ.ም ጀምሮ  እስከ 2015 ዓ.ም ድረስ ላለፉት 44 ዓመታት  በሃርዲ ኮፒ ያለውን   የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት ዲጂታላይዝ ለማድረግ ዩኒቨርሲቲያችን ከትምህርት ቢሮ ጋር በመተባበር  የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት መመዝገቢያና ማደራጅያ ሲስተም በማበልጸግ ወደ ስራ አስገብቷል፡፡ እስካሁንም የ18 ዓመት በላይ  የማጠናቀቂያ ውጤት ዲጂታላይዝ መደረጉ ለማወቅ ተችሏል፡፡

የዚህ ቀጣይ ስራ የሆነው በዛሬው ዕለት የተደገረው የስራ ውል ስምምነት ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል የሚኒስትሪ ፈተና እርማት በሶፍትዌር ለማድረግ የፈተና ወረቀት እርማት ውጤት ማደራጃና ማስተዳደሪያ ሲስተም ለማበልፀግ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ከሁለቱም ተቋማት የሚመለከታቸው የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት የስራ ውል ስምምነት ተፈፅሟል፡፡ 

በዚህ መድረክ ላይ በመገኘት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲያችን የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳነት የሆኑት ዶ/ር ተማም አወል  ዩኒቨርሲቲያችን በምርምርና በቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ ብዙ ስራዎች እያሰራ የሚገኝ መሆኑን ገልፀው ይህ በዓይነትም በይዘትም ልዩ የሆነውን ሲስተም እንድናበለፅግ የትምህርት ቢሮ እድሉን በመሰጠቱ በማመስገን ስራው በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ተጠናቅቆ ወደ ስራ እንደሚገባ አሳውቀዋል፡፡  

የድሬዳዋ አስተዳደር የትምህርት ቢሮ ኃላፊ የሆኑት ክቡር አቶ ሱልጣን አሊይ በበኩላቸው ቢሮቸው የትምህርት ጥራትን ከማስጠበቅ ጎን ለጎን ስራዎችን ዲጂታላይዝ የሚድረግ ስራ በትኩረት እያሰራ መሆኑን በመግለፅ ከዚህ በፊት የበለፀገው እና እየበለፀገ ያለውን ሲስተም ሶፍትዌር ጠቀሜታው እጅግ የጎላ መሆኑን በመግለፅ በቀጣይም ከዩኒቨርሲቲው ጋር በሁሉም ዘርፍ በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡ 

በመጨረሻም የዩኒቨርሲቲያችን  ፕሬዝዳንት የሆኑት ክብርት ዶ/ር ኡባህ አደም ባደረጉት ንግግር በትምህርት ላይ የሚታዩትን ስብራቶች ለመጠገን የሚመለከታቸው አካላት በጋር በትብብር መሰራት እንዳለባቸው በማንሳት በዛሬው ዕለት ሶፍትዌር ለማበልጸግ የተደረገውን የስራ ውል ስምምነት ውጤታማ እንዲሆን አስፈላጊውን ድጋፍ እና ክትትል እንደሚደረግ በማሳወቅ በሌሎችም ጉዳዮች ላይ ከትምህርት ቢሮ ጋር በትብብር ለመስራት ዩኒቨርሲቲው ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

Share This News

Comment