Logo
News Photo

በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ የተቋርጦ የነበረውን የሳይት ስራ ለማስጨረስ ከቻይና CCECC ተቋረጭ ጋር ውል ተፈራረመ፡፡

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በ2011ዓ.ም አስጀምሮት የነበረውና በስራ ተቋረጭ የውል ግዴታ መፈጸም ባለመቻል በ2014 የተቋርጠው የአጥር እና የሳይት ወርክ ግንባታ ፕሮጅክት ስር የነበረውን የሳይት ወርክ ስራ ለማስቀጠል ዛሬ ጥር 24 2016 ዓ.ም ከቻይና ሲቪል ኢንጅነሪግ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ጋር ውል ገብቷል።


የሳይት ወርክ ስራው በውስጡ የ1.5 ኪ.ሜ ርዝመት ያለው የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ግንባታ ያለው ሲሆን ከመንገድ ስራው ጋር ተያያዥ የሆኑ የጎርፍ መውረጃ ቦይ እና የመንገድ መብራት ስራዎች ተካተውበታል። ከዚህም በተጨማሪ የዩንቨርሲቲውን የምድር ገፅ ዲዛይን መሠረት ባደረገ መልኩ አደባባዮች እንዲሁም የአረንጓዴ ስፍራዎችን በከርቭ ስቶን የማካለል ስራ ተካተውበታል።

Share This News

Comment