Logo
News Photo

‹‹አድዋን ለዘላቂ ሠላምና ለጠንካራ-መንግስት ግንባታ›› በሚል መሪ ቃል የምክክር መድረክ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

‹‹አድዋን ለዘላቂ ሠላምና ለጠንካራ-መንግስት ግንባታ›› በሚል መሪ ቃል ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከሰላም ሚ/ር ጋር በመተባበር እና ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ የምክክር መድረክ በዩኒቨርሲቲው አዳራሽ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ በመድረኩ ላይ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች የእንኳን ደህና መጣችሁ እና የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል፡፡ የሃይማኖት አባቶች፣የአገር ሹማግሌዎች፣ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ መምህራን፣ የአስተዳር ሰራተኞች እና ተማሪዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

የአድዋ ድል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ክብር ማኅተም፤ የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ተጋድሎ ቀንዲል የኢትዮጵያ ህዝቦች ታላቅ ድል በአገር አቀፍ ደረጃ ከጥር 14-23/2016 ዓ.ም እየተከበረ ይገኛል፡፡

የውይይት መድረኩ ለአንድ ቀን የሚቆይ ሲሆን በዚሁ መድረክ ላይ አድዋን ለዘላቂ ሠላምና ለጠንካራ-መንግስት ግንባታ እና የጋራ እሴቶቻችን ለዘላቂ ሠላምና ለጠንካራ-መንግስት ግንባታ ላይ የተመለከቱ ሁለት ጥናታዊ ጽሁፎች በምሁራን ቀርበው ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡

በዚህ የውይይት መድረክ ላይ ቁልፍ መልዕክት ያቀረቡ የሚገኙት ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ ሲሆኑ በሃይማኖት አባቶች፣ በአገር ሹማግሌዎችና በዩኒቨርሲቲው ምሁራኖች ልምዳቸውን በማካፈል ረገድ ያለው ፋይዳ የጎላ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡

Share This News

Comment