Logo
News Photo

"በምህንድስናዊ ዘዴ የተሰላ፣ በተሞክሮዎች የታጀበ ምርምርና ትንተና" በሚል መሪ ቃል በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ውይይት ተካሄደ።

በምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዝዳንት የተዘጋጀው "በምህንድስናዊ ዘዴ የተሰላ፣ በተሞክሮዎች የታጀበ ምርምርና ትንተና" በሚል መሪ ቃል በውይይቱን መርሀ-ግብር ላይ ንግግር ያደረጉት የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር መገርሳ ቃሲም የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግራቸው ምህንድስና ሰፊ የሙያ ዘርፍ እንደመሆኑ በውስጡ ብዛት ያላቸው ሌሎች የሙያ ዘርፎችን እንደሚይዝ ገልጸዋል፡፡


ምህንድስና መሰል ተዛማጅ ጉዳዮችን በመመርመር እና ጥራትን የሚከታተል ዘርፍ መሆኑን አንስተዋል። ዩኒቨርሲቲው በምህንድስና ዘርፍ ከፍተኛ ባለሙያን በማሰልጠን በዘርፍ ያለውን ከፍተኛ የሰው ኃይል እጥረት ለመቅረፍ አይነተኛ ሚና እንዳለው በምህንድስና ትምህርት ፕሮግራም ብቁ ተማሪዎችን በማሰልጠን ጊዜው የሚፈልገውን ብቁ ዜጋ በማፍራት ሰፊ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ 


በዚህ የውይይት መድረክ ላይ ተጋባዥ እንግዳ የሆኑት ኢንጂነር ባንተይሁን ትዛዙ በካናዳ ቶሮንቶ ነዋርነቱን ያደረገ የዘርፉ ተመራማሪ ለውይይቱ ተሳታፊ መምህራንና ተማሪዎች ገለጻ አድርገዋል፡፡ እንጂነር ባንተይሁን እንደገለጹት ምህንዲስና ለዘላቂ የልማት ግቦች ዋነኛ መሳሪያ መሆኑን አንስተው አገራችን የምትፈልገው የተማረ የሰው ኃይል እና ኢኮኖሚውን ለማሻሻል ቀጣይነት ያለውን ዕድገት ለማምጣት እና በአርቴፊሻል ኢንተለጀንሲ በመታገዝ ውጤታማ ስራ መስራት እንደሚቻል ተናግሯል፡፡ ከተሞቻችን በዘመናዊ ምህንድስን በማዘመን አረንጓዴ ኢኮኖሚን በተሻለ በመፍጠርና በመጠቀም ዘርፉን ማሳደግ እንደሚቻል አጽኖት በመስጠት አብራርተዋል፡፡ 


በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ጥያቄዎች ተነስተው ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥቶበት ውይይቱ ተጠናቋል፡፡

Share This News

Comment