Logo
News Photo

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛውን ዙር ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና መስጠት መጀመሩን አስታወቀ፡፡

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ሁለተኛ ዙር ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና በተያዘለት መርሀግብር መሠረት መስጠት መጀመሩን የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶ/ር መገርሳ ቃሲም ገልጸዋል፡፡ ዶ/ር መገርሳ ቃሲም አያይዘው በዛሬው ዕለት 239 (ሁለት መቶ ሰላሳ ዘጠኝ) የህክምናና ጤና ሳይንስ ተማሪዎች ፈተናው መውዳቸውን ገልጸዋል፡፡ ዛሬ የተሰጠው የመውጫ ፈተና ያለምንም ችግር በተያዘለት መርሀግብር መሰረት የተሰጠ መሆኑን ገልጸው  ዩኒቨርሲቲው አስቀድሞ በቂ ዝግጅት ማድረጉን ነው ዶ/ር መገርሳ ያሳወቁት። 


የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ቅበላ፣ የአካዳሚክ ሪከርድ እና አልሙኒ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ጂብሪል አብዱልቃድር  እንዳሳወቁት ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ከማክሰኞ የካቲት 6/2016 ዓ.ም አስከ ፊታችን እሁድ የካቲት 11/2016 ዓ.ም ድረስ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በአጠቃላይ በ55 የትምህርት አይነቶች ፈተናው የሚሰጥ መሆኑን ገልፀው ባጠቃላይ 1,186 (አንድ ሺ አንድ መቶ ሰማንያ ስድስት) ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ ይጠበቃል ብለዋል፡፡


ዶ/ር ጂብሪል አያይዘው የመውጫ ፈተናውን ለመፈተን በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በኩል በ8 የትምህርት አይነቶች  ቁጥራቸው 239 (ሁለት መቶ ሰላሳ ዘጠኝ) ተማሪዎች ለማስፈተን እቅድ መያዙን ገልጸው የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲን የመፈተኛ ጣቢያቸው እንዲሆን የመረጡ ከግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከሪፍትቫሊ ዩኒቨርሲቲ፣ ከአዲስ አበባ ሜዲካልና ቢዝነስ ኮሌጅ፣ ከሲቲ ሜዲካልና ቢዝነስ ኮሌጅ፣ ከኪያመድ ኮሌጅ እና ከሉሲ ኮሌጅ ሁለተኛውን ዙር ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና በሚቀጥሉ ቀናቶች እንደሚፈተኑ አሳውቀዋል። 

Share This News

Comment