Logo
News Photo

9ኛው ዙር ሀገር አቀፍ የምርምር ኮንፍረንስ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

9ኛው ዙር ሀገር አቀፍ የምርምር ኮንፍረንስ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ “Synergizinig Business, Health and Technology & Engineering for Sustainable Development” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ይገኛል፡፡ በዚህ ለአንድ ቀን በሚቆየው ሀገር አቀፍ የምርምር ኮንፍረንስ ላይ ዶ/ር ኡባህ አደም የዩኒቨርሲቲያችን ፕሬዝዳንት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዝዳንት የሆኑት  ዶ/ር ተማም አወል የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፋል፡፡ 


በኮንፍረንሱ ላይ ዶ/ር ሰለሞን ቢኖር የትምህርት ሚኒስቴር የምርምርና ማኅበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክተር፣ ዶ/ር ይትባክ ተክሌ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ፣ ዶ/ር ስለሺ ግርማ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ እንዲሁም ፕሮፌሰር ዳንኤል ቅጣው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲውት ቁልፍ መልዕክቶቻቸውን አቅርበዋል፡፡


በዚህ በዩኒቨርሲቲያችን ለ9ኛ ጊዜ እየተካሄደ በሚገኘው ሀገር አቀፍ የምርምር ኮንፍረንስ ላይ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተሳተፉ ጥናት አቅራቢዎች የምርምር ስራዎቻቸውን እያቀረቡ ይገኛሉ፡፡ ኮንፍረንሱ ከሰዓት በኋላም በሶስቱም የመስክ ልየታ ዘርፎች በተለያዩ አዳራሾች የሚቀጥል መሆኑን ከወጣው ፕሮግራም ለመረዳት ችለናል።


Share This News

Comment