Logo
News Photo

አስደሳች ዜና ለድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት የካቲት 01/2016 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ለዶ/ር ሙሉጌታ ግርማ ድብቁ የተባባሪ ፕሮፌሰር የማዕረግ እድገት አጽድቋል፡፡  

የዩኒቨርሲቲው የሴኔት አባላቱ ባደረጉት ስብሰባ፣ አዲሱ የመምህራን ደረጃ እድገት መመሪያ መሰረት የተባባሪ ፕሮፌሰር የማዕረግ ዕድገት ለመስጠት በትምህርት ክፍል፤ ኮሌጅና በSPARC ፀድቆ የቀረበላቸውን ጥያቄ በመመርመር የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ማርኬቲንግ ትምህርት ክፍል መምህር ለሆኑት ዶ/ር ሙሉጌታ ግርማ የተባባሪ ፕሮፌሰር (Associate Professor in Applied Management) ማዕርግ ዕድገት ሰጥቷል፡፡  

ዶ/ር ሙሉጌታ ለአስራ ሶስት አመታት በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ፣ ማርኬቲንግ ት/ት ክፍል መምህርና ተመራማሪ በመሆን ዩኒቨርሲቲውን ስያገለግሉ የቆየ ሲሆን ከመማር ማስተማር ስራዎች ባለፈ በምርምርና ማበረሰብ አገልግሎት ላይ ጉልህ አስተዋጽኦ አበርክተዋል፡፡ በተጨማሪ በዩኒቨርሲቲው የተለያዩ ቋሚ እና ጊዜያዊ ኮሚቴ አበላ ሆነው በማገልገል፤ ለዩኒቨርሲቲው ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጾ ያበረከቱ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ Harla Journal of Sustainable Development in Business and Economics (HJSDBE) Editor in Chief በመሆን እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡   

ዩኒቨርሲቲው ዶ/ር ሙሉጌታ ግርማ ባገኙት የደረጃ ዕድገት እንኳን ደስ አለዎት እያለ መልካም ምኞቱን ይገልጻል፡፡

Share This News

Comment