Logo
News Photo

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ጋር...

በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እና በኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት መካከል በሀገር ዓቀፍ ደረጃ በሚከናወነው የህንፃ ግንባታ ስራዎች የሰው ኃይልና የማሽነሪዎች ምርታማነት ጥናት ፕሮጀክት ላይ ተሳታፊ የሚያደርግ የሁለት ሚለዩን ብር የማማከር ስራ ውል ተፈረመ፡፡ 

የኢትዩጵያ ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት የሀገራችንን የኮንስትራክሽን ዘርፍ ለማዘመን እና ተወዳደሪ ለማድረግ የተቋቋመ ሲሆን በሀገራችን በህንፃ ግንባታ ስራዎች ላይ ከዋጋና የማጠናቀቂያ ጊዜ አወሳሰን ጋር በተያያዘ የሚታየውን ወጥነት የሌለው አሰራር በዘላቂነት ለመቅረፍ ከሚረዱ ግብዓቶች መካከል አንዱ የሆነውን የሰው ኃይልና የማሽነሪዎች ምርታማነት መረጃ እንደ ሀገር በሳይንሳዊ መንገድ ለማጥናት ተወዳድረው ካለፉት ሰባት ዩኒቨርሲቲዎች መካከል ዩኒቨርሲቲውን በመወከል የተሳተፈው የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ከኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂና ማኔጅመንት ት/ክፍል ስምንት መምህራንና ሰላሳ የሚሆኑ ተማሪዎችን ተሳታፊ ያደረገ የጥናት ቡድን በማቋቋም በድሬዳዋና አካባቢዋ ጥናቱን በስድስት ወር ውስጥ ለማከናወን  ከኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ጋር ውል ተፈራርሟል፡፡

በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም እንደገለጹት ችግር ፈች ስራዎችን ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር መዘጋጀቱ እጅግ ጠቃሚ እንደሚሆን በመግለፅ ለጥናት ቡድኑ የስራ መመሪያ ሰጥተዋል።

የኢንስቲትዩቱ ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር የሆኑት ቴዎድሮስ ገደፋየ እንደገለጹት ተጨማሪ ችግር ፈች ፕሮጀክቶችን በተለያዩ ዘርፎች ለማከናወን ኢንስቲትዩቱ እቅዶ እየሰራ መሆኑን በመግለጽ ውጤታማ የሆነ የስራ ጊዜ እንዲሆን ከወዲሁ መዘጋጀት እንደሚገባ ተናግረዋል።

Share This News

Comment