Logo
News Photo

በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ  386 ተማሪዎች ዛሬ ተመረቁ፡፡

በዛሬው እለት የተመረቁት ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ የትምህርት መስኮች በቅድመ ምረቃና በድህረ ምረቃ መርሃግብር በመደበኛና በምሽቱ ክፍለ ጊዜ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ 386 ተማሪዎች ናቸው፡፡

ከእነዚህ ተማሪዎች መካከል 338 ተማሪዎች በቅድመ ምረቃ 29 ተማሪዎች ደግሞ በድህረ ምረቃ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ቆይተው በዛሬው እለት የተመረቁ መሆናቸውን በስነ-ስርዓቱ ላይ ተገልጿል፡፡


በዛሬው እለት በቅድመ መረቃ ለምረቃ የበቁት ተማሪዎች ከህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ፣ ከማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ  እንዲሁም ከቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ትምህርታቸውን በሚገባ ተከታትለው ያጠናቀቁ ተማሪዎች ናቸው ፡፡


በዚህ መሠረትም ከህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በህክምና ዶክትሬት 23  ፣በሜዲካል ላብራቶሪ 29 ፣ በሚድዋይፈሪ 36 ፣በነርሲንግ 34፣ በሳይካትሪ ነርሲንግ 26 ተማሪዎች ሲመረቁ፣ ከማኅበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ በፖለቲካል ሳይንስና አለምአቀፍ ግንኙነት ትምህርት 40 ተማሪዎች መመረቃቸውን በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር መገርሳ ቃሲም በምርቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ገልጸዋል፡፡


ከዚህ በተጨማሪም በቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በኤሌክትሪካልና በኮምፒዩተር ኢንጂነሪንግ 14 ተማሪዎች መመረቃቸውን የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንትፊክ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ቴዎድሮስ ገደፋዬ በምርቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ በዝርዝር አቅርበዋል፡፡


በመጨረሻም በየትምህርት ክፍላቸው የላቅ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የሜዳሊያ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡


Share This News

Comment