Logo
News Photo

" ዓድዋ፤ የኢትዮጵያ እና የጥቁር ህዝቦች የሉዓላዊነት መገለጫ" በሚል መሪ ቃል 128ኛው የዓድዋ ድል በዓል በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በፓናል ውይይት ተከበረ፡፡

128ኛው የዓድዋን ድል በዓል በማስመልከት የድሬድዋ ዩኒቨርሲቲ የማኅበረሰብ አገልግልት ዳይሬክቶሬት ከዩኒቨርሲቲው የታሪክና ቅርስ አስተዳደር ትምህርት ክፍል ጋር በመተባበር  የፓናል ውይይት ተካሄደ፡፡


በዚሁ በዓል ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው የማኅበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ ዲን የሆኑት ዶ/ር መዓዛሽወርቅ እርገጥ ሲሆኑ በንግግራቸው የአሁኑ ትውል የቀደመ ታሪኩን በቅጡ ተረድቶ በዓድዋ ድል የተገኙ የድል ቱሩፋቶች ማስቀጠል እንዲችል ከምሁራን ብዙ እንደሚጠበቅ ገልጸው ለዚህም ኮሌጁ በቀጣይ የተለያዩ መድረኮችን በማዘጋጀት የተለያዩ የግንዛቤ መፍጠሪያ እንቅስቃሴዎችን የሚያርግ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡


በፓናል ውይይቱ ላይ የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ተማም አወል የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በንግግራቸውም የዓድዋ ድል በዓል ጀግኖች አባቶቻችን በተባበረ ክንድ ወራሪውን የፋሺሽት ኃይል ቅስም በመስበር ድል ነስተው  የሀገራችንን ክብር ማፅናት የቻሉበት በዓል መሆኑን አስታውሰው ዛሬም የሀገራችን ጠላቶች ከየአቅጣጫው ተሰልፈው መጠነ ሰፊ የጥፋት ዘመቻ ስለከፈቱብን ሁላችንም ከቀደሙት ጀግኖች አባቶቻችን የተረከብናትን ሀገር ለመጪው ትውልድ ለማስረከብ ከመቼው ጊዜ በበለጠ ክንዳችንን አስተባብረን  በአንድነት መቆም ይጠበቅብናል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ 

  

በፓናል ውይይቱ በታሪክና ቅርስ አስተዳደር ት/ት ክፍል መምህራን 'Islam-state Relation and the Battle of Adwa (1889- 1896)' በመምህር አብዱልከሪም ተመስገን እንዲሁም 'Adawa Victory Centenary Commemoration: Scholars and Politicians/EPRDF Government Discourses,1996' በመምህር ናትናኤል ለምለም ሁለት ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

Share This News

Comment