Logo
News Photo

በህግ ጥላ ስር ለሚገኙ ታራሚዎች የልብስ ስፌት ስልጠና መስጠት ተጀመረ፡፡

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በፌደራል ማረሚያ ቤት አስተዳደር በድሬደዋ ማረሚያ ቤት ለሚገኙ 30 ታራሚዎች ነው የልብስ ስፌት ስልጠናው መሰጠት የተጀመረው፡፡

በኢንስቲትዩቱ የቴክስታይልና አፓሬል ፋሽን ዲዛይን ትምህርት ቤት አጠቃላይ ቁጥራቸው 30 ለሚሆኑ በህግ ጥላ ስር ለሚገኙ ታራሚዎች የሚሰጠው የልብስ ስፌት ስልጠና ለተከታታይ 30 ቀናት የሚቆይ ነው፡፡

በስልጠናው መክፈቻ ላይ የኢንስቲትዩቱ ሳይንትፊክ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ቴዎድሮስ ገዳፋዬ እንዳሉት ዩኒቨርሲቲው በእስከ ዛሬው በማኅበረሰብ አቀፍ አገልግልቱ በርካቶችን ተጠቃሚ ያደረገ ተግባራትን አከናውኗል፡፡

ኢንስቲትዩቱ በቀጣይም በተለያዩ መስኮች ታራሚዎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራትን ያከናውናሉ ያሉት አቶ ቴዎድሮስ በተለይም ታራሚዎች የተጣለባቸውን የቅጣት ጊዜ አጠናቀው ወደ ህብረተሰቡ ሲቀላቀሉ ሥራ ፈጣሪ በመሆን  ከራሳቸው አልፈው ሌሎችንም መጥቀም  እንዲችሉ የሚደረገው ድጋፍና እገዛ ይቀጥላል ብለዋል፡፡


በፌደራል ማረሚያ ቤቶች የድሬደዋ ማረሚያ ቤት ኮምሽን ም/ኮምሽነር ወንድሙ ደበላ በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው ከዚህ ቀደምም የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሰው በተለይም ታራሚዎችን በሞያ ለማብቃት የሚደረጉ ድጋፎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ማረሚያ ቤቱ ብዙዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ በሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች  ዩኒቨርሲቲው የበኩሉን ድጋፍ እንዲያደርግ በዚሁ ወቅት ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡


በመጨረሻም የዩኒቨርሲቲው የልዑኳን ቡድን በማረሚያ ቤቱ ታራሚዎች እየተከናወኑ የሚገኙ የምርትና የልማት ሥራዎች ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡


Share This News

Comment