Logo
News Photo

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፣ከኢትዪጵያ ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣንና ከድሬድዋ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ።

ድሬ ድዋ ዪኒቨርሲቲ በቅርስ ጥበቃ በባህል ጥናትና የቱሪዝም ልማትን ጨምሮ በታላላቅ ሀገራዊ ፍይዳ ባላቸው ጉዳዮች ላይ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝ በመግለጽ፤ የከተማ አስተዳደሩን የቅርስ የባህል ልማትና ቱሪዝም ዘርፋ ላይ ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት በሚያደርገው ጥረት ውስጥ ዩኒቨርስቲው ከተቋማቱ ጋር በመሆን ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ በላቀ ደረጃ  ውጤታማ ስራዎችን ለማከናወን ስምምነቱ አስፈላጊ መሆኑን የድ.ድ.ዩ የም/ቴ/ሽ ም/ል ፕሬዝዳንት ተማም አወል (ዶ/ር) ገልጸዋል። በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ የነበሩት የድሬድዋ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሚካኤል እንዳለ በበኩላቸው ከድ.ድ.ዩ ና የኢ.ቅ.ጥ.ባ ጋር በጋራ በመስራት በአሰተዳደሩ እየተሰሩ ላሉትና ለታቀዱ የቅርስ ጥበቃ ባህልና ቱሪዝም ዘርፍ ላይ በምርምር ቴክኖሎጅ ሽግግር እና በዘርፉ የለውጥ ተግባራትን እውን እንዲሆኑ ለማስቻል በሚደረገው ጥረት ላይ ስምምነቱ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ገልጸዋል። በመጨረሻም የኢ.ቅ.ጥ.ባንም የተለያዩ ስራዎችን አብረን እየሰራን ቢሆንም በሰነድ በተደገፈ ውል ስራችንን መስራት የታቀደ ውጤታማ የሆነ ስራ ለማከናወን ይረዳናል ብለዋል።

Share This News

Comment