Logo
News Photo

ሦስተኛው የብዝሐነት ፎረም "በብሔራዊ ምክክርና ሰላም ግንባታ ዘላቂ ልማትን ማረጋገጥ" በሚል መሪ ቃል በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ተከበረ፡፡

ፎረሙን በንግግር የከፈቱት የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም ኢትዮጵያ ከ80 በላይ  ብሔር ፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መኖሪያ  በመሆኗ የብዝሐ ባህሎችና ቋንቋዎች በውስጣ አቀፋ እንድትይዝ አስችሏታል፡፡

ይህ  ፀጋ ደግሞ ብዙዎች እንዲኖራቸው የሚመኙት ግን የሌላቸው ታላቅ ፀጋ መሆኑን ተገንዝበን ለሀገር ዘላቂ ሰላም መስፈንና ለተፋጠነ ልማት ከዛም ከፍሲል ለሀገር እድግትና ለሁለንተናዊ ለውጥ መምጣት ልንጠቀምብት ይገባል፡፡

ነው ያሉት ዶ/ር ኡባህ ታዲያ   ይህንን ብዝሐነት ያጎናፀፈን ፀጋ  ተገንዝብን ለታላቅ አገራዊ ፋይዳ በማዋል ዘላቂ ሰላምን በማረጋገጥ በቅጡ መጠቀም የእኛ ፋንታ ነው ብለዋል፡፡

ብዝሐነትን በማከበር ማስተናገድ መጀመራችን አንዱ የስልጡን ህዝቦች መገለጫ ነው ያሉት ዶ/ር ኡባህ ብዝሐነት በአንድ አገር  የዲሞክራሲያዊ ስርዓት ለማስፈን ሙሉ ፍላጎት መኖሩን አንዱ ማሳያ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

 መስፈን አንዱ ማሳያ መሠልጠንተጠቅመን በሀገራችን ዘላቂ ሰላም በማረጋገጥ ልማትን በማፋጠን ትርጉም ያለው እድግትና ለውጥን በማስመዝገብ የህዝባችን ኑሮ እንዲሻሻል ሁላችንም የበኩላችን ድርሻ ልንወጣ ይገባል፡፡

በልዩነታችን ውስጥ በአንድ ላይ ተዋህዶና ተቀይጦ የሚገኘውን ውብ አንድነታችን ከማጠናከር አንኳያ የምሁራን ሊወጡት የሚገባው ኃላፊነት ከሌሎች ትንሽ ከፍ ያለ ነው፡፡

ይህንን ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባትም ምሁራን  የተለያዩ ጠቃሚ ጥናትና ምርምር ሥራዎች በብዛትና በጥራት በማበርከት ልዩነትን የግጭትና የመጠፋፋት ምክንያት ሆነው አሁን አሁን ላይ በድንግት ብቅ ብለው የሚታዩትን ከፋፋይ ትርክቶች እንዲጠሩ ከማድረግ አንፃርም ድርብ ኃላፊነት አለባቸው ብለዋል፡፡

ምሁራኑ ይህንን ሀገራዊ ኃላፊነት አንግበው በተለይም ከቅርብ ወራት በኋላ ለማካሄድ በእቅድ ይዘን እንቅስቃሴ የጀመርንበት ብሔራዊ ምክክር ስኬታማ እንዲሆን  የበኩላችንን ኃላፊነት ሊወጡ ይገባል በማለት አስገንዝበዋል፡፡

በዚሁ ፎረም ላይ ተገኝተው የፎረሙን ታዳሚዎች እንኳን ደህና መጣችሁ ያሉት በዩኒቨርሲቲው የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ተማም አወል በአገርአቀፉ ደረጃ የብዝሐነት ፎረምን  የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከዛሬ ሦስት ዓመት ጀምሮ አንዴም ሳይቋረጥ ለተከታታይ ሦስት ዓመታት ማለትም ለ3ኛ ጊዜ  በማዘጋጀት እንዲከበር አድርጓል፡፡

የአሁኑ ፎረም በዩኒቨርሲቲው ሲዘጋጅ በልዩነታችን ውስጥ ያለውን አንድነታችንን አጠናክረን የሀገራችን መፂዕድል የተቃና በድል ቱሩፋቶች የታጀበ እንዲሆን ለማድረግ ብዝሐነታችን ለአንድነታችን መጠናከር ያለውን የላቀ ጥቅም ግንዛቤ እንዲወሰድብት ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በዚሁ ፎረም ላይ የተለያዩ ምሁራን ብዝሐነትና አማራጭ የግጭት መፍቻ ባህላዊ የግልግል እሴቶችን የተመለከቱ ፅሁፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸው ፎረሙ ተጠናቋል፡፡


Share This News

Comment