Logo
News Photo

አለም አቀፉ የሴቶች ቀን በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ በፓናል ውይይት ተከበረ፡፡

የፓናል ውይይት ተካፋይ ተሳታፊዎችን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት ንግግር ያደረጉት በዩኒቨርሲቲው የሴቶችና ወጣቶች ፣ ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ/ እና ልዩ ፍላጎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ዝናሽ ደሳለኝ የአለም አቀፉ የሴቶች ቀን (March 8) በአለም አቀፍ ደረጃ ለ113 ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ46ኛ ጊዜ " ሴቶችን እናብቃ ሰላምና ልማትን እናረጋግጥ" በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በዩኒቨርሲቲ ደረጃም ቀኑን በማስመልከት የፓናል ውይይት መዘጋጀቱን ጠቁመው በፓናሉ ላይ ለውይይት መነሻ የሚሆን ፅሁፍ በዩኒቨርሲቲው ምሁራን ቀርቦ ውይይት የሚደረግበት መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

በፓናል ውይይቱ ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በዩኒቨርሲቲው የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዝዳንት ተወካይ ረ/ፕሮፌሰር ይታገሱ ስንታየሁ ሴቶች ለዘመናት በዘለቁ የተዛቡ አስተሳሰቦችና አመለካከቶች  ሳቢያ ለተለያዩ ጫናና ጭቆናዎች ሲዳረጉ ቆይተዋል፡፡

ይህ ደግሞ ሴቶችን ለበርካታ ውስብስብ ችግሮች በመዳረግ መብታቸው ተገፎ ከምጣኔሃባታዊው ፣ ከማኅበራዊው ተጠቃሚነት ተነፍገው  እና  ከፖለቲካው መድረክ የተገለው የቆዩበትን አስቸጋሪ ዘመን ለማሳለፍ ተገደዋል፡፡

በፈረንጆቹ 1907 ዓ.ም ላይ ሴቶች በዩናይትድ ስቴስት ኦፍ አሜሪካ አደባባይ በመውጣት ተቃውማቸውን ከሰሙ በኋላ ግን ይሄው የሴቶች የመብት ጥያቄ በተቀረው የአለም ክፍልም ተሰራጭቶ ሴቶች ይድርሱባቸው የነበሩት ጫናዎችና ጭቆናዎች ቀስ በቀስ እየቀነሱ እንዲመጡ ማድረግ ተችሏል፡፡


እንደ ረ/ፕሮፌሰር ይታገሱ ገለፃ በዩኒቨርሲቲው የሴቶችን ተጠቃሚነትና ተሳታፊነት የሚያሳድጉ በርካታ ተግባራት ተከናውነዋል ያሉ ሲሆን በተለይም ካለፋት ሦስት ዓማታት ወዲህ ሴቶች ላይ  ትኩረት ተደርገው የተከናወኑት ተግባራት ውጤታማ ነበሩ፡፡ 

በተለይም ለሴት የትምህርት አመራሮችና በተለያዩ የአስተዳደር እርከን ላይ የሚገኙ ሴቶችን የመፈፀም አቅም ከማሳደግ  አንፃር ተከታታይነት ያላቸው የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎች ሲሰጡ መቆየታቸውንና ይነዚህ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎች በቀጣይም ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል፡፡

በፓናል ውይይቱ ላይ በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ቤት መምህርና እጩ ዶክተር ህሊና አሸናፊ (The role of Empowering Women and achieving Gender Equality to the sustainable development of Ethiopia) በሚል ርዕስ  ለውይይት መነሻ የሚሆን ፅሁፍ አቅርበዋል፡፡

Share This News

Comment