Logo
News Photo

ሴት ተመራማሪዎች ሴቶች ካሉባቸው ውስብስብ ችግሮች ሊያላቅቁ አቅም ያላቸው የተግባራዊ የምርምር ሥራዎች ትኩረት ሊያደርጉባቸው ይገባል ተባለ፡፡

በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በሴት ተመራማሪዎች እና አገር በቀል ዕውቀት ላይ ትኩረታቸውን ያደረጉ 17 ትልመ ጥናቶች ቀርበው የተገመገሙበትን መድረክ በንግግር የከፈቱት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም ናቸው፡፡

ዶ/ር ኡባህ በንግግራቸው እንደገለጹት ሴት መምህራን በምርምር ሥራዎች ላይ ያላቸውን ተሳትፎ ለማሳደግ በርካታ ሥራዎች ተሠርተዋል፡፡

በተለይ ዩኒቨርሲቲው ከባለፈው 3 ዓመት ወዲህ የሴት መምህራንን በምርምር ሥራዎች ላይ የሚያደርጉትን ተሳትፎ ለማሳደግ የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ ነበሩ ብለዋል፡፡

"ሴት ተመራማሪዎች በዕለት ተዕለት ከሚገጥሟቸው ችግሮች ተነስተው ተግባራዊ የምርምር ሥራዎች ላይ ትኩረት አድርገው ቢሠሩ ውጤታማ ይሆናሉ" ሲሉ ተናግረው እነዚህ ሥራዎች ወደ ማኅበረሰቡ ወርደውና ተተግብረው መልሰው ማኅበረሰቡን ተጠቃሚ እንዲያደርጉ ሴቶች ድርብ ኃላፊነት አለባቸው ያሉት ዶ/ር ኡባህ ሴት ተመራማሪዎች በተለይ ሴት እህቶቻቸው ካሉባቸው ውስብስብ ችግሮች ተላቀው መብታቸውና ተጠቃሚነታቸው እንዲረጋገጥ የአቅማቸውን ጥረት ማድረግ ይኖርባቸዋል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡


በተመሳሳይ በዚሁ መድረክ ላይ ቀርበው ከሚገመገሙት 17 ትልመ ጥናቶች መካከል ገሚሶቹ አገር በቀል ዕውቀት ላይ ያተኮሩ መሆናችውን በዩኒቨርሲቲው የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ተማም አወል ተናግረዋል፡፡

ዶ/ር ተማም ትልመ ጥናቶቹ ወደ መሬት ወርደው ማኅበረሰቡን ተጠቃሚ እንዲያደርጉ ዩኒቨርሲቲው በቻለው አቅም ሁሉ ድጋፍን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

አገር በቀል ዕውቀቶቻችንን ከዘመናዊው ጎን ለጎን እያስኬድን ለሀገር ልማትና እድግት ልንጠቀምብት ይገባል በማለት አስገንዝበዋል፡፡


በዕለቱ በሴት መምህራንና አገር በቀል ዕውቀቶች ላይ ያተኮሩት 17ቱ ትልመ ጥናቶች ቀርበው በመድረኩ ተሳታፊዎች ተገምግመዋል፡፡

Share This News

Comment