Logo
News Photo

የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር የከተሞች ገቢ ሪፎርም ፕሮጀክት ጽ/ቤት ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ከአራት ክልሎች ለተውጣጡ ባለሙያዎች በከተማ መሬትና ፕላን ዘርፍና የሙያ ብቃት ማረጋገጫን አስመልክቶ ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡

በስልጠናው ማጠናቀቂያ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር መገርሳ ቃሲም በንግግራቸው አገራችን ያለመችውን ዕድገት ለማረጋገጥ ብሎም ከተሞችን ከተረጅነት ነፃ ለማውጣ በመሬትና መሬት ነክ ላይ ራሳቸውን በፋይናንስ ዘርፍ አቅም እንዲኖራቸው ለማስቻል የሰለጠኑ ብቁ የሆኑ የሰው ኃይል እንደሚያስፈልግ ተናግሯል፡፡ ዶ/ር መገርሳ አያይዘው ከሀብቶች ሁሉ የላቀውን ሀብት ትርጉም ባለው ሂደት ለማዘመንና ከዘርፉ ሊገኝ የሚገባውን ገቢ ለማስገኘት ብቁ ሙያተኞች ስለሚያስፈልጉት ይህ ስልጠና መሰጠቱን ተናግረዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው ፍትሃዊ የሆነ የመሬት አስተዳደር እንዲኖር ከሚ/ር መ/ቤቱ ጋር የጀመረውን ግኑኝነት አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑንም አረጋግጠዋል፡፡


በዚሁ የስልጠና መዝጊያ ፕሮግራም ላይ በመገኘት ለሰልጣኞቹ የስራ መመሪያ ያስተላለፋት የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር የከተሞች ገቢ ሪፎርም ፕሮጀክት ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ዚነት ኢብራሂም በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት በከተማ መሬት ልማትና ፕላን ዘርፍ ከአፋር፣ ከሶማሌ፣ ከሐረሪ ክልላዊ መንግስት እና ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የተመረጡ የዘርፉ ባለሙያዎች በአራት የስልጠና ዘርፎች ከደረጃ II እስከ V የሙያ ደረጃዎች አሰልጥኖ እና የሙያ ብቃት ምዘና ሲኦሲ ለሶስተኛ ጊዜ ከማዕከል በተላከው የስልጠና ቲኦቲ መሰረት የተዘጋጀ መሆኑን አንስተዋል፡፡ አያይዘውም ሰልጣኞች በተግባር ንድፈ-ሀሳብ የተደገፈ ስልጠና በስኬት ሰልጥነው እንዲበቁ ላበረከታችሁ አካላት በሙሉ የላቀ ምስጋናቸውን አቅርበው ከዩኒቨርሲቲው ጋር በቀጣይ በጋራ እንደሚሰሩ ተናግረዋል። 


በስልጠናው መርሀ ግብር ላይ የመዝግያ ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንሲቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ገደፋዬ ባስተላለፉት መልዕክት ሰልጣኞች ለስልጠናው በተቀመጠው መስፈርት መሰረት በተግባርና በንድፈ-ሀሳብ የተደገፈ ስልጠና ወስዳችሁ መብቃታችሁ በከተሞች መሬት አስተዳደር ዘርፍ የሚታየውን የመልካም አስተዳደር ችግሮች በመቅረፍ ሳይንሳዊ መርህን በመከተል የአከባቢያችሁን የከተማ መሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ስርዓት በማዘመን ከተሞች ያላቸውን የመሬት ሀብት በአግባቡ አውቀው በእቅድ እንዲመራና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት እንዲሁም በስልጠናው ያገኛችሁትን ዕውቀት በመተግበር ህዝቡና መንግስት ከዘርፉ ማግኘት ያለበትን ጥቅም ለማስጠበቅ በትጋት መስራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡፡

Share This News

Comment