Logo
News Photo

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ማህበራዊና ልማት ኮሚሽን የሐረር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ጋር የስልጠና ውል ተፈራረመ

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ማሕበራዊና ልማት ኮሚሽን የሐረር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከ30 ዓመታት በላይ ልምድ ያለው አገር በቀል መንግሥታዊና ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ሲሆን አጋሩ ከሆነው Catholic Relief Service ኢትዮጵያ ጋር በመሆን በበርካታ ዘርፎች በዩ.ኤስ.አይ.ዲ የተደገፈ ለአምስት አመት የሚቆይ Resilient Food Security Activity (RFSA)/Ifaa ፕሮጀክትን ተግባራዊ በማድረግ የቤተሰብ ምግብ እና ስነ-ምግብ ደህንነትን ለማሻሻል የሚያስችሉ ፕሮጀክቶችን የሚሰራ ድርጅት ነው፡፡ 


ዩኒቨርሲቲው ከድርጅቱ ጋር የተፈራረመው ውል ከምስራቅ ሀረርጌ ወረዳዎች የተውጣጡ ሥራ አጥ ወጣቶችን በተለይም ሴቶች እና አካል ጉዳተኞች ላይ ያተኮረ ለ90 ቀናት (3 ወራት) የሚዘልቅ የስራ እድልን የሚፈጥር በጨርቃጨርቅና አልባሳት ክህሎት ላይ የሚያተኩር ሥልጠናን ለመስጠት ሲሆን፤ ስልጠናው በተግባር የተደገፈ እና የስራ ፈጠራ ክህሎቶችን የሚያስጨብጥ እንደሚሆን ይጠበቃል።

Share This News

Comment