Logo
News Photo

በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ  60 የተጠናቀቁ የምርምር ስራዎች ቀርበው ተገመገሙ፡፡

በዩኒቨርሲቲው የተጠናቀቁ የምርምር ስራዎች ለመገምገም የተዘጋጀውን መድረክ በንግግር የከፈቱት በዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር መገርሳ ቃሲም በዩኒቨርሲቲው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የመምህራን በጥናትና ምርምር ስራዎች ላይ  ያላቸው ተሳትፎ ጨምሯል፡፡

በዩኒቨርሲቲው የሚቀርቡ የምርምር ስራዎች ከወትሮው በተለየ መልኩ በቁጥርም ሆነ ከጥራት አንፃር በከፍተኛ መጠን ማሳደግ የተቻለበት ነው፡፡

ዩኒቨርሲቲው  በልየታ የአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ዘርፍ የተለየ ከመሆኑ አንፃር በመምህራኖች የሚሰሩ የምርምር ስራዎች ከኢንዱስትሪ ተቋማት ባለሙያዎች እና ከሌሎች አካላት ጋር በጥምረት ተሰርተው ሃብት ማምጣት አለባችሁ በማለት አፅኖት በመስጠት አሳስበዋል፡፡ 

የሚሰሩ የምርምር ሥራዎች ለህትመት በቅተው የመንግስትና የማኅበረሰቡን ችግር መፍታት እንዲችሉ ተመራማሪዎች በግልም ሆነ በጋራ ጥረታቸውን ማስቀጠል እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው የምርምር ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ረ/ፕሮፌሰር ይታገሱ ስንታየሁ በበኩላቸው  ለሁለት ቀናት በሚቆየውና በዳይሬክቶሬቱ አዘጋጅነት የሚካሄደው የምርምር ሥራዎች የግምገማ መድረክ ላይ ከህግ ኮሌጅ በስተቀር ሁሉም ኮሌጆች የተሳተፉበትና ከ60 በላይ የተጠናቀቁ የምርምር ስራዎች ቀርበው የሚገመገሙበት ነው ብለዋል፡፡ 

ረ/ዳት ፕሮፌሰር ይታገሱ አክለውም በዩኒቨርሲቲዉ ታሪክ ከፍተኛው ቁጥር የያዘ የምርምር ሥራዎች በአንድ መድረክ ላይ የቀረበበት መሆኑን ገልጸው በአለም አቀፍ ደረጃ የታመነበትና ለመጀመሪያ ጊዜ 24 ምርምሮች በፖስተር የቀረቡ መሆኑን ተናግረዋል። 

ለሁለት ቀን በቆየው መድረክ ላይ ከ60 በላይ  የተጠናቀቁ የምርምር ሥራዎች ቀርበው የተገመገሙ ሲሆን በቀጣይም እነዚህን የተጠናቀቁ የምርምር ሥራዎች ወደ መሬት ወርደው መተግበር እንዲችሉ አስፈላጊው ሁሉ ጥረት በዩኒቨርሲቲው በኩል እንደሚደረግ በመድረኩ ማጠናቀቂያ ፕሮግራም ላይ ተገልጻል፡፡


Share This News

Comment