Logo
News Photo

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ 8ኛውን የኢትዮጵያ ሕግ ትምህርት ቤቶች ምስለ-ችሎት ውድድር አሸናፊ ሆነ!

8ኛው የኢትዮጵያ ሕግ ትምህርት ቤቶች ምስለ ችሎት ውድድር ከመጋቢት 20-22/2016 ዓ.ም በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ እና በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትህና ሕግ ኢኒስቲትዩት የጋራ አዘጋጅነት በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የተካሄደ ሲሆን የድሬዳዋ ዩኒቨርሲት ሕግ ኮሌጅ በዛሬው ዕለት በተካሄደው የፍፃሜ ውድድር መድረስ የቻለ ሲሆን በአምስት ዳኞች በተሰጠው ድምር ውጤት መሰረት የውድድሩ አሸናፊ ሆኗል። 


ውድድሩ ለሁሉም የኢትዮጵያ ሕግ ትምህርት ቤቶች ክፍት የሆነ ሲሆን የቃል ክርክሩ ላይ የሚሳተፉ ዩኒቨርሲቲዎች በውድድሩ የፅሁፍ ዙር ባስመዘገቡት ውጤት የተመረጡ ናቸው። 


የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ኮሌጅም የውድድሩ አሸናፊ በመሆን የውድድሩን ዋንጫ  ከማንሳቱ  ተጨማሪ ሶስት ዋንጫዎችንና አንድ ልዩ ሽልማት ማሸነፍ ችሏል። 


ውድድሩ ለይ የተሳተፉ ተማሪዋች፦

1. ተማሪ ምህረት ወንድሙ

2. ተማሪ ማህሌት ወርቅነህ

3.  ተማሪ ሰብለ ገሰሰ ሲሆኑ መምህር ዓለምሰገድ ደጀኔ ደግሞ የተማሪዋቹ አሰልጣኝ በመሆን ተሳትፏል። 


በውድድሩም ተማሪ ምህረት ወንድሙ የውድድሩ የመጀመሪያ ዙር ምርጥ ተናጋሪ፣ የመጀመሪያው ዙር ምርጥ ሴት ተናጋሪ፣ የፍፃሜ ዙር ምርጥ ተናጋሪ እና የአጠቃላይ ውድድሩ ምርጥ ተናጋሪ በመሆን ውድድሩን በበላይነት በማጠናቀቅ 3 ዋንጫዎችን እና የልዩ ሽልማት አሸናፊ ሆናለች። 


በአጠቃላይ ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ለውድድሩ ከተዘጋጁት 5 ዋንጫዎች 4ቱን በማሸነፍ ውድድሩን በበላይነት አጠናቋል።

Share This News

Comment