Logo
News Photo

ድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ከድሬዳዋ አስተዳደር ንግድ እና ኢንዱስትሪ ቢሮ ጋር በመተባበር የሰራው የ10 አመት አምራች የኢንዱስትሪዎች ፍኖተ ካርታ ሰነድ ዝግጅት የመጀመሪያው ዙር ግምገማ ተከናወነ፡፡

ዩኒቨርሲቲው ከድሬዳዋ አስተዳደር ጋር ከሚሰራቸው ስራዎች መካከል የሆነው የአምራች ኢንዱስትሪዎች የ10 አመታት ፍኖተ ካርታ ስራ ላለፉት ስድስት ወራት በዩኒቨርሲቲው ባሙያዎች ሲጠና የቆየ ሲሆን በተቀመጠለት የግዜ ሰሌዳ መሰረት ተጠናቆ የመጀመሪያ ዙር ግምገማ ተካሂዷል፡፡ ሰነዱ በአስተዳደሩ ያለውን አሁናዊ የኢንዱስትሪዎች ሁኔታ፣ የባለድርሻ አካላት ግምገማ፣ የኢንዱስትሪ ስትራቴጂ እንዲሁም የማስፈፀሚያ ስልቶችን ያካተተ ሲሆን በሁለት የተለያዩ ቀናት በተደረገው የግምገማ መድረክ ላይ የሚመለከታቸው የዩኒቨርሲቲው ሃላፊዎች፣ የንግድ እና ኢንዱስትሪ የቢሮ ሃላፊዎች፣ ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እንዲሁም ሌሎች ተቋማት የተውጣጡ ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

Share This News

Comment