Logo
News Photo

በማህበረሰብ ጉድኝት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሠጠ። ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

የድሬ ዳዋ  ዩኒቨርሲቲ የማኅበረሰብ  ተሳትፎ ዳይሬክቶሬት በማህበረሰብ ጉድኝነት ዙሪያ ለዩኒቨርሲቲው መምህራንና በየርከኑ ለሚገኙ ኃላፊዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ፡፡


የስልጠናው ዓላማ የማኅበረሰብ ጉድኝነት ፅንሰ ሃሳብና አተገባበር ላይ ግንዘቤ መፍጠር እንዲሁም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚያፈሯቸው ምሩቃን የማኅበረሰቡን ችግር ከማወቅና ከመፍታት አንጻር የእውቀት ክህሎትና አመለካከት ይዘው እንዲወጡ የሚስችል የማስተማር ሥነ-ዘዴ አስፈላጊነት ላይ ያተኮረ ነው፡፡


ስልጠናውን የሰጡት በአሜሪካው ኮሎራዶ ስቴት ዩኒቨርሲቲ የረጅም ግዜ የማስተማር ልምድ ያካባቱት ፕሮፌሰር አሰፋ ገ/አምላክ ሲሆኑ በስልጠናው ያደጉ ሃገራት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የትምህርት ሥርዓታቸውን ከማህበረሰቡ ፍላጎት ጋር በማጣጣም ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው የማህበረሰቡን ችግር መሰረት ያደረገ የመማር ማስተማር ዘዴ ሂደት ውስጥ የሚልፉበትን ተሞክሮዎች በማቅረብ የሃገራችን የከፍተኛ ትምህርት አሰጣጥ የሚሻሻልበትን መንገዶች አመላክተዋል፡፡


በስልጠናው ላይ የተሳተፉ አንዳንድ መምህራን ስልጠናውን በተመለከተ አስተያየታቸውን የሰጡ ሲሆን ስልጠናው በማኅበረሰብ ጉድኝት ዙሪያ ረጅም አመት ልምድ ባላቸው ምሁር በመሰጠቱ ብዙ ልምድ እንዳገኙበት ገልጸው  ዩኒቨርሲቲው በቀጣይ መሰል ስልጠናዎችን በማዘጋጀት መምህራን በትምህርት ሥርዓቶችና በማስተማር ሥነ-ዘዴ ላይ ለውጥ ለማምጣትየሚያስችል እውቀትና ክህሎት  እንዲጨብጡ እንዲያደርግ ጠቁመዋል።

Share This News

Comment