Logo
News Photo

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ማህበራዊና ልማት ኮሚሽን የሐረርጌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ከምስራቅ ሀረርጌ ወረዳዎች የተውጣጡ ሥራ አጥ ወጣቶችን ተቀብሎ በጨርቃጨርቅና አልባሳት ክህሎት ስልጠና መስጠት ጀመረ፡፡

ዪኒቨርሲቲው ከኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ማሕበራዊና ልማት ኮሚሽን የሐረርጌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር  ከምስራቅ ሀረርጌ አራት ዞኖች እና አስር ወረዳዎች ለተውጣጡ ለ50 ሥራ አጥ ወጣቶች  የስራ እድልን የሚፈጥር በጨርቃጨርቅና አልባሳት ክህሎት ላይ የሚያተኩር ሥልጠናን ለመስጠት  ዛሬ የማስጀመሪያ ፕሮግራም አከናውኗል፡፡ 


በፕሮግራሙ ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንት ዶ/ር ኡባህ አደም  እንደተናገሩት ዩኒቨርሲቲው  ካሉበት ሃላፊነቶች መካከል  የማህበረሰብ አገልግሎት አንዱ ሲሆን ዛሬ የተጀመረው ስልጠና የገጠሩን ወጣቶች ተደራሽ የሚያደርግ በመሆኑ ደስታ እንደተሰማቸውን  ተናግረዋል፡፡  ዩኒቨርሲቲውም ለስልጠናው ስኬት የተቻለውን ሁሉ እንደሚያደርግ ገልጸው ለሰልጣኞች መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የኮሚሽኑ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ግርማ ከበደ ስለተቋማቸው እና ስለፕሮግራሙ ገለፃ አድርገው ሰልጣኞች ያገኙትን እድል በአግባቡ እንዲጠቀሙ እና ውጤታማ የስልጠና ጊዜ እንዲያሳልፉ አሳስበዋል፡፡ በመቀጠልም ንግግር ያደረጉት ወ/ሮ ጥሩሴት ሀይሌ የስርአተ-ጾታ የወጣቶችና ማህበራዊ ዳይናሚክስ ም/ኃላፊ እንደተናገሩት ፕሮግራሙ ለወጣቶች በተለይም ለሴቶች ትልቅ ትኩረት መስጠቱ እጅግ ለየት እንደሚደርገው ገልፀው ሰልጣኞች እንዴት ውጤታማ ግዜ ማሳለፍ እንደሚችሉ ምክራዊ መልዕታቸውን አስተላልፈዋል፡፡


በመክፈቻ ፕሮግራሙ ከአራቱም  የምስራቅ ሀረርጌ ዞኖች እና አስር ወረዳዎች የተጋበዙ እንግዶች፣ የኢንዱስትሪ ተወካዮች፣ የዩኒቨርሲቲው የስራ ሃላፊዎች እና ሌሎች የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የተሳተፉ ሲሆን፤ ለሶስት ወራት በሚቆው ስልጠና ላይ 39 ሴቶች እና 11 ወንዶች ተሳታፊ እንደሚሆኑ ታውቋል፡፡

Share This News

Comment