Logo
News Photo

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት “የሁለተኛ ዙር ሴሚናር” አካሄዷል

በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ከምርምር እና ህትመት ቢሮ ጋር በመተባበር የግማሽ ቀን የሁለተኛ ዙር ሰሚናር ያካሄደ ሲሆን በኘሮግራሙ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የኢንስቲትዩቱ ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ተወካይ የሆኑት አቶ ቴዎድሮስ ገደፋየ በፕሮግራሙ ለተጋበዙ ተሳታፊዎች የእንኳን ደህና መጣቹ እና የመክፈቻ ንግግር ካደረጉ በኋላ ሴሚናር ለምርምር፣ ቴክኖሎጂ ሽግግር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ባህል ለመሳደግ የሚጠቅም በመሆኑ ኢንስቲትዩቱ አጠናክሮ እንደሚሰራ ገልጸዋል።

የምርምር ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክተር ቢሮ ተወካይ የሆኑት ዶ/ር ግርማ ቤካ በበኩላቸው የሴሚናር አላማ እና ጥቅሞች ዙሪያ በንግግራቸው ያነሱ ሲሆን የሴሚናሩ ዋና አላማው መምህራን የምርምር ባህላቸው እንዲያሳድጉ እና ተሳታፊ እንዲሆኑ እንደሚያግዝ ከገለጹ በኋላ የት/ቤቶች ሃላፍዎች ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ፣ የድህረ ምረቃ ተማርዎችም ሴሚናር እንዲያቀርቡ እና ተሳታፊ እንዲሆኑ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ዶ/ር ግርማ ቤካ አክለው ሴሚናሩ ብዙ መምህራን የተሳተፉበት እና የምርምር ባህል ለማሳደግ የላቀ ሚና እንደሚኖረው ገልፀው መምህራን የምምር ባህላቸው እንደሚያሳድጉ እምነታቸው እንደሆነ ገልፀዋል።

Share This News

Comment