Logo
News Photo

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከሀረሪ ክልል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ጋር የፕሮጀክት ስምምነት ተፈራረመ፡፡

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ  ከሀረሪ ክልል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ጋር በመተባበር የወንጀል መዝገብ መረጃ እና አስተዳደር ስርዓት “Crime Record Information and Management System (CRIMS)” የሚል ሶፍትዌርን ለማበልፀግ ስምምነት አድርጓል፡፡ ፕሮጀክቱ በኢፌዲሪ ፍትህ ሚኒስቴር የወንጀል ሪከርድ መረጃና አስተዳደር ሥርዓት  መነሻነት የሀረሪ ክልልን ህጋዊ አሰራርን ለማዘመን የታለመ የለውጥ ስራ ሲሆን በሀገር ደረጃ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስርዓቱን ተከትሎ  በተቋሙ አጠቃላይ ዲጂታል ለውጥ እቅድ አካል ነው፡፡   ስርዓቱ በወረዳ ደረጃ ክስ ከመጀመሩ ጀምሮ በዐቃቤ ህግ የወንጀል ክስ እስከመቅረብ ድረስ አጠቃላይ ሂደቱን የሚያቀላጥፍ ሲሆን በወረዳም ሆነ በክልል ያሉ ወንጀሎችን እንደ ዝርፊያ እና አደንዛዥ እፅ ዝውውር ያሉ ጉዳዮችን ጨምሮ የሚቆጣጠር ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ፕሮጀክቱ 1.5 ሚሊዮን ብር ወጪ የሚደረግበት ሲሆን በስድስት ወራት ውስጥ የሚጠናቀቅ ይሆናል፡፡

Share This News

Comment