Logo
News Photo

ለስድስት ተከታታይ ቀናት ወደኢንኩቤሽን ማዕከል ለሚገቡ ሰልጣኞች ሲሰጥ የነበረው የስታርት አፕ ስልጠና ተጠናቀቀ።

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጲያ ልማት ኢንስቲትዩት እና ከኢትዮጵያ ስራ ፈጣሪ ወጣቶች ማኅበር ጋር በመተባበር ከዩኒቨርሲቲው ከተለያዩ ትምህርት ክፍሎች ለተውጣጡ  ወጣቶች ለስድስት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የነበረው  “Design Your Venture” የተሰኘ የስታርት አፕ ስልጠና ተጠናቀቀ።

ስልጠናው ከኢትዮጲያ ልማት ኢንቲትዩት በመጡ በዘርፉ ልምድ ባላቸው አሰልጣኞች የተሰጠ ሲሆን የተሻለ የቢዝነስ ሀሳብ ያላቸው 40 ተማሪዎች ተመርጠው ተሳትፈውበታል፡፡

ስልጠናውን ያጠናቀቁት ወጣቶች በቀጣይ የፈጠራ ስራቸውን ወደገበያ ለማውጣት እንዲረዳቸው ወደኢንኩቤሽን ማዕከል የሚገቡ ሲሆን ሃሳባቸውን ወደተግባር አውርደው ውጤታማ እንዲሆኑ ተከታታይ ድጋፍ እንደሚደረግላቸው ይጠበቃል፡፡


Share This News

Comment