የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በዋንኞቹ የዕቃ መጋዘኖች ውስጥ ካይዘንን ተግባረዊ በማድረግ በርካታ ሃብትን ከብክነትና ከብልሽት ማዳን መቻሉን አስታውቋል፡፡
በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም የካይዘን ትግበራው ያለንን ውሱን ሃብት ከብክንትና ከብልሽት በመጠበቅ የተሰጠንን ተልዕኮ ለማሳካት የጀመርነውን ጉዞ የቀና እንዲሆን ማድረግ የቻለ ነው፡፡
አሁን ላይ የተገኘውን መልካም ተሞክሮ ወደ ተቀሩት ክፍሎች በማስፋት ሀብትን ከብክነትና ከብልሽት ለማዳን የበኩላቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
በዩኒቨርሲቲው የአስተዳደርና ልማት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሰለሞን ዘሪሁን በዚሁ የምረቃ ስነ-ስርዓት ተገኝተው ንግግር ያደረጉ ሲሆን ካይዘንን ተግባራዊ በማድረጋችን የአገልግሎት ቅልጥፍና፣ ከንብረት ብክነትና ብልሽት እንዲሁም ከንብረት አስተዳደርና አላስፈላጊ ወጪን ከመቀነስ አኳያ ውጤታማ ሥራ መስራት ችለናል ብለዋል፡፡
በምረቃ ስነ-ስርዓት ላይ ለ2 ወር በቆየው ሥራ የነበሩ ሂደቶች ደረጃ በደረጃ በካይዘን አስተባባሪዎቹ መምህራን የተብራራ ሲሆን ለስራው መሳካት አስተዋፅዖ ለነበራቸው መምህራንና የአስተዳደር ሠራተኞች የእውቅና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል፡፡
Dire Dawa University is found in the industrial and commercial city of Dire Dawa, which is located at 515 km east of Addis Ababa. It is a young higher education institution, established and started its teaching and learning activities in 2007 academic year.
Copyright © 2021, Dire Dawa University. All Rights Reserved.
Share This News