ለዩኒቨርሲቲው ተልዕኮ ስኬት በየደረጃው የሚገኙ የአካዳሚክ ዘርፍ አመራሮች የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ፡፡
የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ በአዲሱ የሥራ መዋቅር መሠረት በአካዳሚክ ዘርፍ ስር በሚገኙ መደቦች ላይ የተለያዩ መምህራን ተወዳድረው መደልደላቸው ይታወሳል፡፡
በዛሬው እለትም ለአዲሶቹ የአካዳሚው ዘርፍ የትምህርት አመራሮች በዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደምና በአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር መገርሳ ቃሲም የሥራ መመሪያ ተሰጥቷል፡፡
በዚሁ ወቅት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም የመማር ማስተማር ተልዕኳችን ቀዳሚ እንደመሆኑ ይህ ተልዕኮ እንዲሳካ በአካዳሚው ዘርፍ በየደረጃው ከሚገኙ የትምህርት አመራሮች ብዙ የሚጠበቅ መሆኑን በንግግራቸው አስገንዝበዋል፡፡
በዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር መገርሳ ቃሲም በበኩላቸው በከፍተኛ ትምህርት ተቋም የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል የተያዘውን እቅድ ከዳር ለማድረስ የትምህርት አመራሮቹ የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡
በመጨረሻም አዲሶቹ የአካዳሚክ ዘርፍ የትምህርት አመራሮቹ በቅርቡ ተገንብቶ የተመረቀውን የኢ- ለርኒግ መልቲ ሚዲያ ስቱዲዮን ጎብኝተዋል፡፡
Share This News