Logo
News Photo

አዲሱ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ቴክኖሎጂ ማበልፀጊያ መዕከል ተመርቆ ተከፈተ፡፡

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ስራ እድል ፈጣሪዎችን (ስታርታፖችን) የሚያሰለጥንበት እና ሃሳባቸውን ወደ ንግድ የሚቀይሩበት የቢዝነስ እና ቴክኖሎጂ ማበልፀጊያ ማእከል በአዲስ መልክ ተደራጅቶ ተመርቋል፡፡ ማእከሉ ከአንድ አመት በፊት በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ባለ አነስተኛ ስፍራ ለተወሰኑ ወራት ሲሰራ የቆየ ሲሆን በዪኒቨርሲቲው አመራሮች በተሰጠው ትኩረት በተሻለ ስፍራ በአዲስ መልኩ ተደራጅቶ ለምረቃ በቅቷል፡፡ ማዕከሉ ለተማሪዎች፣ ለመምህራን እና በድሬዳዋ ዙሪያ ላሉ ወጣቶች የሃሳብ ማበልፀጊያ ማዕከል ሆኖ የሚያገለግል ሲሆን በአሁኑ ወቅት 14 ስታርታፕ ቢዝነሶችን ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር ወደስራ ለማስገባት እየሰራ ይገኛል፡፡ አዲሱን ማዕከል የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም መርቀው የከፈቱት ሲሆን በፕሮግራሙ ላይ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች ዲኖች ዳሬክተሮች እንዲሁም የማዕከሉ ሰልጣኞች ተገኝተዋል፡፡

Share This News

Comment