Logo
News Photo

የህግ ታራሚዎችን በተለያዩ ሙያዎች በማሰልጠን የተሻሉ ዜጐች እንዲሆኑ የማድረጉ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለፀ፡፡

በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የድሬዳዋ ማረሚያ ማዕከል ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በልብስ ስፌት ያሰለጠናቸውን የህግ ታራሚዎች አስመርቋል፡፡

በተለያዩ ምክንያቶች በህግ ጥላ ስር ሆነው የሚገኙ ዜጐች በማረሚያ ቤት በሚኖራቸው የቆይታ ጊዜ እራሳቸውን በተለያዩ ሙያዊ ክህሎቶች አዳብረው እንዲወጡ እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል።

ይህም ታራሚዎች ከማህበረሰቡ ጋር በሚቀላቀሉበት ጊዜ የተሻሉ ዜጐች እንደሆኑ ከማስቻሉም ባሻገር በገቢ ራሳቸውን እንዲችሉ አይነተኛ ሚና ይጫወታልም ተብሏል፡፡

በታራሚ ሰልጣኞች ምረቃ ወቅት የማረሚያማዕከሉ ዳይሬክተር ረዳት ኮምሸነር ወንድሙ ደበላ እንዳሉት ማረሚያ ቤቱ መሰል ስልጠናዎችን በተለያዩ ጊዜያት ለታራሚዎች ሲሰጥ መቆየቱን አስታውሰው፣ ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ቴክስታይል ትምህርት ክፍል ለታራሚዎች በልብስ ስፌት ዘርፍ የሰጠው ስልጠና በእጅጉ የሚያስመሰግነው ተግባር ነው ብለዋል።

ታራሚዎችም በስልጠናው ያገኙት እውቀት ወደ ተግባር የሚቀየር በመሆኑ ያለ መሰልቸት ሊሰሩበት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ኘሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው እንዲህ አይነት ለማህበረሰቡ የሚጠቅሙ ድጋፎችን እየሰጠ መሆኑን አንስተው በተለይም ለታራሚዎች ነፃ የህግ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

ዶ/ር ኡባህ አክለውም ዩኒቨርሲቲው በትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ለታራሚዎች ሙያዊ ስልጠናዎችን እየሰጠ እንደሚገኝ ጠቅሰው ይህም በቀጣይ በቴክኖሎጂ ዘርፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ቃል ገብተዋል፡፡

ሰልጣኝ ታራሚዎችም በተረደገላቸው የሙያዊ ስልጠና ድጋፍ ጥሩ እውቀትና ክህሎት መጨበጣቸውን ተናግረው ሙያውን በማሻሻል የተሻለ ደረጃ ላይ ለመድረስ እንደሚሰሩም ገልፀዋል፡፡

Share This News

Comment