Logo
News Photo

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እና ገበያ ቴክኖሎጂ ከተባሉ ተቋማት ጋር በጋራ መስራት የሚያስችለውን የስምምነት ሰነድ ተፈራረመ።

በዚህ 10ሺህ ወጣቶችን ስድስት ዩኒቨርሲዎችን ማዕከል በማድረግ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ስራ መፍጠር የሚያስችል ሃገራዊ የክህሎት ስልጠና የማስጀመሪያ መርሀ-ግብር ላይ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እና ገበያ ቴክኖሎጂ ከተባሉ ሁለት ተቋማት ጋር በጋራ መስራት የሚያስችለንን የስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል።

ስልጠናው በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ በጃፓን ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (JICA)፣ በሳፋሪኮም ኢትዮጵያ፣ በሱሚቶም እና በገበያ ቴክኖሎጂ ተቋማት ጋር በጋራ ትብብር የሚከናወን ይሆናል።

ይህንን የስልጠና ፕሮግራም ለማስካት እንደ ማዕከል ሆነው የሚሰሩት ስድስቱ ዩኒቨርሲዎች መቀለ፣ ባህርዳር፣ አዋሳ፣ ድሬዳዋ፣ አዳማ እና ጂግጅጋ ዩኒቨርስቲዎች መሆናቸውን በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ ተገልጿል።

Share This News

Comment