Logo
News Photo

የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ

በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ በኩል የመግባቢያ የስምምነት ሰነዱን የተፈራረሙት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም  የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ኃላፊ ዶ/ር የሺሁን አለማየሁ ናቸው፡፡ በዚሁ ወቅት የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም እንዳሉት ይህ የጋራ ስምምነት መደረጉ ከዩኒቨርሲቲውም አልፎ የምስራቁ የሃገራችን ክፍል የኢንድስትሪ ኮሪደር ለመሆን ርዕይ ለሰነቀችው ድሬዳዋ ከተማ ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖረው ገልፀዋል፡፡ በተጨማሪም የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ በሃገራችን ከሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መካከል የአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ እንዲሆን በተደረገው ልየታ መሠረት እንቅስቃሴ በጀመረበተረ ወቅት ከኢንስቲትዩቱ ጋር ተቀራርቦ መስራቱ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ እስፔስ ሳይንስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሃላፊ ዶ/ር የሺሁን አለማየሁ በበኩላቸው እንደገለጹት ኢንስቲትዩቱ በሰው ኃይል የአቅም ግንባታና በተለያዩ መስኮች ከዩኒቨርሲቲው ጋር በድጋፍ እንዲሁም በትብብር እንደሚሰራ አስታውቀዋል፡፡

በመጨረሻም ከኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ቴክኖሎጂ  ኢንስቲትዩት የመጡት የልኡካን ቡድኖች በዩኒቨርሲቲው የተለያዩ ላብራቶሪዎችን ጎብኝተዋል፡፡


Share This News

Comment