Logo
News Photo

ለተመራቂ የልዩ ፍላጎትና ሴት ተማሪዎች ሽኝት ተደረገ፡፡

ለድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የ2016 ዓ.ም የልዩ ፍላጎትና ሴት ተማሪዎች በተዘጋጀው የሽኝት መርሀግብር ላይ የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር መገርሳቃ ሲም በመገኘት ለተማሪዎቹ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ዶ/ር መገርሳ በመልዕክታቸው ተማሪዎቹ ነገ የሚገጥማቸውን ፈተና ሁሉ ተቋቁመው ከራሳቸው አልፈው ለሀገር ጠቃሚ ዜጋ መሆን እንዲችሉ ከወዲሁ በቂ ዝግጅት ማድረግ አለባቸው ብለዋል፡፡

በዩኒቨርሲቲው የሴቶችና ወጣቶች ፣ ልዩ ፍላጎትና ኤች.አይ.ቪ ኤድስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ ዝናሽ ደሳለኝ ለልዩ ፍላጎትና ሴት  ተማሪዎች የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደረግ ቆይቷል፡፡

በተለይም ለተመራቂ  የልዩ ፍላጎትና ሴት ተማሪዎች የመውጫ ፈተናን በስኬት ማጠናቀቅ እንዲችሉ የተለያዩ የስነ-ልቦና የኮንፒዩተር ስልጠና እንዲያገኙ ሲደረግ መቆየቱን ጠቁመው ይሄው ተግባር በቀጣይም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

በዚሁ የሽኝት ፕሮግራም ላይ መምህር ሠላማዊት ተማሪዎቹ በቀጣይ በሥራ ቅጥርና በህይወታቸው ላይ ሊገጥማቸው የሚችሉ ፈተናዎችን እንዴት ማለፍ ይችላሉ በሚሉና በተያያዥ ርዕሶች ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና ተሰጥቷቸዋል፡፡

Share This News

Comment