Logo
News Photo

የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ የገና በዓልን አስመልክቶ የሃገርን ሰላም ለማስከበር በግንባር እየተዋደቁ ለሚገኙ የዘማች ቤተሰቦች የምግብ ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ፡፡

ለዘማች ቤተሰቦች ድጋፍ በተደረገበት ወቅት የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም እንደገለፁት ዩኒቨርሲቲውና መላው የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ የሃገርን ህልውና ለማስጠበቅ ተጋድሎ እያደረገ ላለው ለጀግናው የመከላከያ ሠራዊትና በጦርነቱ ሳቢያ ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን የተለያዩ ድጋፎችን ማድረጉን ገልፀዋል፡፡

በዛሬው እለትም በክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች ዘንድ የሚከበረውን የገና በዓል ምክንያት በማድረግ ለዘማች ቤተሰቦች የተለያዩ የምግብ ቁሳቁሶች ድጋፍ መደረጉን ገልፀውአሁን የተደረገው ድጋፍ ከዘማች ቤተሰቦች ጋር መተዋወቂያ ነው ያሉት ዶ/ር ኡባህ በቀጣይም ዩኒቨርሲቲውና መላው የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ለዘማች ቤተሰቦች የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

ዶ/ር ኡባህ በመጨረሻም በዩኒቨርሲቲ ደረጃ የተቋቋመውን በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ምላሽ ግብር ሀይል ላደረጉት እንቅስቃሴ ሁሉ በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ስም ምስጋና አቅርበዋል።

በዩኒቨርሲቲው የምርምርና ማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶ/ር ሰለሞን ዘርሁን በበኩላቸው ለዘማች ቤተሰቦች የተደረገው የምግብ ቁሳቁቀስ ድጋፍ የዘይት፣ የፓስታ እና የዱቄት ድጋፍ መሆኑን ጠቅሰው በቅርቡም የንጽህና መጠበቂያ የፈሳሽ ሳሙና ድጋፍ ለማድረግ ዩኒቨርሲቲው ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ተናግረዋል፡፡

ድጋፉን ሲረከቡ ያገኘናቸው የዘማች ቤተሰቦች በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው በዚህ አስቸጋሪ ወቅት እነሱን አስታውሶ ድጋፍ ማድረጉ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው መሆኑን በመግለፅ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

Share This News

Comment