Logo
News Photo

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም በተማራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና በተሸለ ሁኔታ ተማሪዎችን ማሳለፍ ለቻሉ የኮሌጆችና የትምህርት ክፍሎች እውቅና ተሰጠ፡፡

በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር መገርሳ ቃሲም ተማሪዎች በመውጫ ፈተና የማለፊያ ውጤት ማምጣት እንዲችሉ የመምህራን ድርሻ የጎላ መሆኑን ጠቅሰው የተሻለ አፈፃፀም ማስመዝገብ ለቻሉ ኮሌጆችና የትምህርት ክፍሎች እውቅና መስጠት ማስፈለጉን አሰታውቀዋል፡፡

በቀጣይም ለመምህራን እውቅናና ማበረታቻ የመስጠቱ ተግባር ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ም/ፕሬዝዳንቱ ዶ/ር መገርሳ ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም ለትምህርት ክፍሉ ኃላፊና ተወካይ ለሆኑት መምህራን የእውቅና የምስክር ወረቀት ከዩኒቨርሲቲው የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዝዳንት እና የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ተወካይ ከዶ/ር ተማም እጅ ተቀብለዋል፡፡


Share This News

Comment