የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በመረጃና መገናኛ ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት በICT Academy በኩል የሚሰጠው Cisco Academy፣ Huawei Academy ፣ Complete Web-Based Apps Using Framework፣ Android App Development from Scratch፣ Advanced Computer, Printers and Copy Machines Maintenance፣ Computer Application and Digital Literacy ከተግባር ተኮር ስልጠና ጋር በበቂ ሁኔታ በማደራጀት ለመስጠት ተዘጋጅቷል።
በመሆኑም IT Essential, CCNA (CCNA 1: Introduction to Networks, CCNA 2: Switching, Routing and Wireless Essentials and CCNA 3: Enterprise Networking, Security and Automation) ፣ Huawei HCIA-Datacom እና ከላይ የተገለጹትን ጠቃሚ ስልጠናዎችን ለመውሰድ የምትፈልጉ በቅድሚያ የስልጠና እና የመመዝገቢያ ክፍያ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000014301503 ክፍያ በመፈጸም እና የከፈሉበትን ደረሰኝ በሚመዘገቡበት ወቅት ማያያዝ እንዳለባችሁ እያሳውቅን ከታች በተገለጸው ድህረ-ገጽ ሊንክ ላይ በመግባት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን የመመዝገቢያ ጊዜ ከመስከረም 13 እስከ መስከረም 23/2016 ዓ/ም ድረስ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
Registration link
Share This News