Logo
News Photo

የፌደራል መንግስት ሰራተኞች አዋጆች ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና ለድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ሰራተኞች መስጠት ተጀምሯል፡፡

ስልጠናው በዋነኝነት ትኩረት ያደረገው የፌደራል መንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2010 ፤የዲስፒሊን ክስ እና መልስ አሰጣጥ እንዲሁም የዲስፒሊን አፈፃፀም እና ቅሬታ አቀራረብ ደንብ ቁጥር 77/1994 በተመለከተ ለዩኒቨርሲቲው የቤተ- መጽሐፍት ሰራተኞች እየተሰጠ መሆኑን የስልጠናው አስተባባሪ ወ/ሮ የውብነሽ ተ/ወልድ ገልፀዋል፡፡

ሰራተኞቹ ስልጠናውን መውሰዳቸው መብትና ግዴታቸውን አውቀው ለአገልግሎት ፈላጊው ማህበረሰብ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያስችላቸው ወ/ሮ የውብነሽ አያይዘው ገለጸዋል፡፡

ለመጽሐፍት-ቤት ሰራተኞች የሚሰጠው ስልጠና የአንደኛ ዙር ስልጠና ሲሆን በቀጣይ በየደረጃው ለሚገኙ የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ሰራተኞች ስልጠናው የሚሰጥ መሆኑን ከወጣው መርሀ-ግብር ለማወቅ ተችሏል፡፡

Share This News

Comment