Logo
News Photo

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በየዓመቱ በሳይንስና ሒሳብ የትምህርት አይነቶች በመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች መካከል የሚያካሂደው የጥያቄና መልስ ዉድድር ተጀምሯል፡፡

የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ስቴም ማእከል (STEM Center) ከዩኒቨርሲቲው የማህበረሰብ ተሳትፎ ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር በየዓመቱ የሚያካሂደውና ትኩረቱን በሳይንስና ሂሳብ የትምህርት ዓይነቶች ላይ ያደረገው የጥያቄና መልስ ውድድር የመጀመሪያው ዙር ውድድር ዛሬ ጥር 6/2014 ዓ.ም ተጀምሯል፡፡ 

እንደሚታወቀው ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በሳይንስና ሒሳብ የትምህርት አይነቶች ከፍተኛ ዝንባሌ ያላቸውንና በምርምር ስራ አዲስ ግኝት መፍጠር የሚችሉ ተማሪዎችን ለማፍራት በሚደረገው ሃገራዊ ጥረት የበኩሉን ድርሻ ለማበርከት ሰፊ እቅድ በመያዝ በድሬዳዋ አስተዳደር የሚገኙ የመንግስትና የግል የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ በሳይንስና ሂሳብ ትምህርት ዙሪያ በመምህራንና ተማሪዎች ላይ እየሰራ ይገኛል፡፡ ዛሬ የተጀመሪው የመጀመሪያው ዙር የጥያቄና መልስ ውድድርም የዚህ እንቅስቃሴ አንዱ አካል ነው፡፡ 

የዚህ ውድድር ዋና አላማ የ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ተማሪዎችን የሳይንስና የሒሳብ ትምህርቶች እዉቀትና ክህሎት ማበልፀግ፤ የመማር ፍላጎት ማነሳሳት እንዲሁም በተማሪዎች መካከል የዉድድር ስሜት መፍጠር እና ግንኙነታቸዉን ማጠናከር ሲሆን በዘንድሮው ዓመት በባለፈው በ2013 ዓ.ም ከነበረው በተሻለ ብዙ ትምህርት ቤቶችና ተማሪዎች የግልንም ጨምሮ ተሳታፊ ሆነውበታል፡፡ ውድድሩ በአራት ዙር የሚከናወን ሲሆን የመጨረሻ አሸናፊዎቹ ልዩ ልዩ የማበረታቻ ሽልማቶችና በዩኒቨርሲቲው የሳ.ቴ.ም.ሂ (ሳይንስ ቴክኖሎጂ ምህንድስናና ሂሳብ) ማዕከል የት/ት እድል የሚሰጥ ይሆናል::

Share This News

Comment