Logo
News Photo

2ኛው ዙር የቬንቸር 360 ፕሮግራም በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ።

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ቴክኖሎጂ ማበልጸጊያ ማዕከል አይስ አዲስ (iceaddis) ከተባለ ሀገር በቀል ተቋም ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ቬንቸር 360 ​​(Venture 360) ፕሮግራም ተካሄዷል። 

ማስተርካርድ ፋውንዴሽን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና አይስአዲስ ከተባለ ተቋም ጋር በመተባበር ቬንቸር ሜዳ፡ በኢትዮጵያ የስራ እድል ፈጠራ  በኢንኩቤሽንና አክስለሬሽን ድጋፍ (Job Creation through Incubation and Acceleration Support in Ethiopia) በሚል ስያሜ ያስጀመረው የአምስት አመት ፕሮጀክት ሲሆን ቁጥራቸው 56,160 የሚሆኑ ወጣቶች የስራ እድል እንዲያገኙ እንዲሁም 100 ስታርታፖችን ማብቃት አላማ ያደረገ ፕሮጀክት ነው። 

ቬንቸር 360 ፕሮግራም የቬንቸር ሜዳ ፕሮጀክት አካል ሲሆን በሀገራችን ኢትዮጵያ በተለያየ የቢዝነስ ስራ በመሰማራት ውጤታማ የሆኑ ስራ ፈጣሪዎች ያላቸውን ልምድ የሚያካፍሉበት ወርሀዊ ፕሮግራም ሲሆን የድሬዳዋ ዮኒቨርሲቲ ቢዝነስና ቴክኖሎጂ መበልጸጊያ ማዕከል ይህንን ፕሮግራም ለሁለተኛ ጊዜ ያዘጋጀ ሲሆን በፕሮግራሙ ላይ የዩኒቨርሲቲያችን የሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ መምህርና የአፍሮኔክስ ቴክ ሀብ መስራችና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት መ/ር ፀጋ እንደሻው 'Startup Thinking, Technology and Innovation 101' በሚል የመነሻ ሀሳብ ያላቸውን እውቀትና ልምድ በእለቱ ዝግጅቱን ለታደሙ ለተማሪዎች አካፍለዋል።  

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ቴክኖሎጂ ማበልጸጊያ ማዕከል ከዚህ ቀደም በአንደኛው ዙር ቬንቸር 360 ፕሮግራም በድሬደዋ ከተማ ታዋቂ የሆነውን የብሉ ዴሊቨሪ (Blu Delivery) ድርጅት መስራች የሆኑትን ወጣት ናትናኤል አለበል እና ወጣት ሮቤል አለማየሁን በመጋበዝ ያላቸውን የቢዝነስ ተሞክሮ ለዩኒቨርሲቲያችን ተማሪዎች እንዲያካፍሉ ማድረጉ ይታወሳል። 

Share This News

Comment