Logo
News Photo

ትምህርት ሚኒስቴር እና ድሬደዋ ዩንቨርሲቲ በ2017 በሚተገበሩ ቁልፍ አፈጻጸመሞች ዙሪያ ውል ተፈራረሙ።

ትምህርት ሚኒስቴር ከሁሉም የመንግስተት ዩኒቨርስቲዎች ጋር በ2017 ዓ/ም በሚተገበሩ ቁልፍ አፈጻጸሞች ዙሪያ ውል የተፈራረመ ሲሆን በድሬደዋ ዩንቨርሲቲ በኩል የዩንቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዶ/ር ኡባህ አደም ውሉን ተፈራርመዋል። 

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በስምምነቱ ወቅት እንደገለጹት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰሯቸው ምርምሮችና የሚያፈሯቸው ዜጎች አገር የሚለውጡና ከዓለም ጋር ተወዳድረው ማሸነፍ የሚችሉ ሊሆኑ ይገባል ብለዋል። ዩኒቨርስቲዎች ራሳቸውን ወደ ራስገዝነት እያሳደጉ እድገታቸውንና ቀጣይነታቸውን ማረጋገጥ እንደሚጠበቅባቸውም ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ተናግረዋል። 

የድሬደዋ ዩንቨርሲቲ ፕሬዝደንት ዶ/ር ኡባህ አደም በበኩላቸው ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር የተፈራረሙትን ዕቅድ ወደ ተግባር ለመቀየር ከመላው የዩንቨርሲቲው ማህበረሰብ ጋር በመሆን ተግተው እንደሚሰሩ ጠቅሰው በቁልፍ የአፈጻጸም መለኪያ ስምምነቱ መሠረት ውጤት የሚያስመዘግቡ ተቋማት በበጀት ጭምር የበለጠ የሚደገፉበት፣ ዝቅተኛ አፈጻጸም የሚያስመዘግቡት ደግሞ ተጠያቂ እንደሚሆኑ ጠቁመዋል። 

በቀጣይም በሀገር ደረጃ የተፈረመው የቁልፍ አፈጻጻም አመላካች ሰነድ ወደ ተቋም በማውረድ በየዘርፉ ካሉ ምክትል ፕሬዝዳንቶች እንዲሁም ታች እስከ ግለሰብ ድረስ የሚቀጥል መሆኑንም ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ በመጥቀስ የዩንቨርሲቲው አመራር፣ መምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞች ዩንቨርሲቲው የተሰጠውን ተልዕኮ ለማሳካት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ እንዲዘጋጁ አሳስበዋል።

Share This News

Comment