Logo
News Photo

የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የአቻ ለአቻ ውይይት የሚካሂዱበት መዕከል በይፋ ተከፍቶ አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡

የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲው ባለፈው ነሃሴ ወር ላይ የማህበራዊ አገልግሎት ጤና ልማት ድርጅት ( OSSHD )ከተባ ግብረ ሰናይ ደርጅት ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችለውን የጋራ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሞ ወደ ስራ መግባቱ ይታወሳል፡፡

በዚህ መሠረትም የኤች .አይ.ቪ ኤድስ እና የስነ-ተዋልዶ ጤና ችግር ተጋላጭነትን ለመቀነስ ታሳቢ ያደረገ እንቅስቃሴዎች የተጀመረ ሲሆን የዩኒቨርሲቲው የሴቶችና ወጣቶች ፣ ኤች.አይ.ቪ. /ኤድስ/ና ልዩ ፍላጎት ዳይሬክቶሬት ከ( OSSHD) ጋር በመተባበር  ያደራጀው መዕከል በይፋ ተከፍቶ ለተማሪዎች አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡

በዩኒቨርሲቲው የሴቶና ወጣቶች ፣ ኤች. ኤይ.ቪ ኤድስና ልዩ ፍላጎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ ይታገሱ ፍቃዱ የመዕከሉን መከፈትን አስመልክቶ እንደተናገሩት ዳይሬክቶሬቱ የተማሪዎችን የኤች .አይ .ቪ ኤድስ ተጋላጭነትንና የስነ-ተዋልዶ ጤና ችግር ለመቅረፍ የተለያዩ ተግባራት ከአጋር አካልት ጋር እያከናወኑ መሆኑን ገልፀው OSSHD ከተሰኛው አገር በቀል ግብረ ሰናይ ደርጅት ባገኘው የተለያዩ ቁሳቁሶች ድጋፍም መዕከሉ ሊከፈት መቻሉን ተናግረዋል፡፡

የመዕከሉ መከፈትም ተማሪዎች አርስ በእርስ በመማማር ራሳቸውን ከኤች አይ .ቪ ኤድስና ከስነ-ተዋልዶ ጤና ችግር መጠበቅ የሚያስችላቸው  ሲሆን ከዚህ ጎን ለጎንም እየተዝናኑ እውቀት መገብየት የሚችሉበት ምችችቶች በመዕከሉ የተደራጁ መሆናቸውንም ጨምረው ገልፀዋል፡፡

በመጨረሻም በዚሁ የመክፈቻ ፕሮግራም ላይ የተገኙ 16 ሴትና 8 ወንድ ተሳታፊዎች   የኤች. አይ.ቪ ኤድስ የደም ምርመራ ማድረጋቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

Share This News

Comment