Logo
News Photo

ተማሪዎች በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የሚያደርጉት የምክክር መርሃ ግብር በድሬደዋ ዩንቨርሲቲ ተጀመረ

የድሬደዋ ዩንቨርሲቲ ከኢትዮጲያ የህግ /ርት ቤቶች ህብረት፣ ከአሜሪካን ህዝቦች የእርዳታ ተቋም (USAID) እና ዓለማቀፍ ኢሌክቶራል ፋውንዴሽን (IFES) ጋር በመተባበር የተማሪዎች ውይይት መርሃ ግብርን አስጀምሯል።

የውይይት መርሃ ግብሩን መርቀው ያስጀመሩት የዩንቨርሲቲው አካዳሚክ /ፕሬዝዳንት / መገርሳ ቃሲም እንደተናገሩት ሁሉም የሰው ልጆች ያለምንም ልዩነት የሚፈልጉት ትልቁ ጉዳይ ሰላም ነው። ሰላምን የምንሻውን ያህል ደግሞ ሰላም እንዲሰፍን ሁላችንም የበኩላችንን ሚና ልንጫወት ይገባል’’ በለዋል። / መገርሳ በመቀጠል ውይይት ሰላም እንዲሰፍን ትልቅ ሚና ይኖረዋል ዩንቨርሲቲያችንም ይህንን የተማሪዎች የውይይት መርሃ ግብር ከተባባሪ አካላት ጋር ሲያዘጋጅ የውይይትን ፋይዳ በመረዳት ነው ሲሉ ተናግረዋል።

የኢትዮጲያ የህግ /ርት ቤቶች ህብረት ድሬደዋ ዩንቨርሲቲን ጨምሮ ከሌሎች 6 ዩንቨርሲቲዎች ጋር ስለሚተገብረው የተማሪዎች ምክክር ገለጻ ያደረጉት ደግሞ የህግ /ርት ቤቶች ማህበር ጀኔራል ማናጀር አቶ ደርሶልኝ የኔአባት ናቸው። አቶ ደርሶልኝ አሁን ከድሬደዋ ዩንቨርሲቲ ጋር በመተባበር ያስጀመሩት የተማሪዎች ውይይት ለሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ተማሪዎቹ በሚያደርጉት ውይይት የሚቀጥል መሆኑን አውስተው ውይይቱ በተማሪዎች መሀል ቅርርብ እንዲፈጠር፣ የመነጋገር ባህላችን እንዲዳብር እና የተለያዩ ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ያግዛል ብለዋል።

የድሬደዋ ዩንቨርሲቲ ህግ /ርት ቤት ዲን የሆኑት / ዘነበ ሞሼ በበኩላቸው የተማሪዎቹ ውይይት እንዲደረግ ከፍተኛ እገዛ ያደረጉ አካላትን አመስግነው ውይይቱን ለማድረግ የተመረጡ ተማሪዎች እና አስተባባሪዎች ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲወያዩ ጥሪ አስተላልፈዋል። በውይይቱ 70 የዩንቨርሲቲው ተማሪዎች የሚሳተፉ ሲሆን ውይይቱን እንዲያስተባብሩ ደግሞ 10 የተመረጡ ተማሪዎች ምኖራቸውን በውይይት ማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ ተጠቅሷል።

 

Share This News

Comment